Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከዘይድ ቢን ኻሊድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 56 languages
«ከዘይድ ቢን ኻሊድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በአላህ መንገድ የሚዘምትን ያሰናዳ ሰው በርግጥም ዘምቷል። በአላህ መንገድ ለዘመተ ሰው (ቤተሰብ) በመልካም ትብብሩ የተተካ በርግጥም ዘምቷል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ለሚዘምት ሰው መሳሪያ፣ መጓጓዣ፣ ምግብ፣ ቀለብና ሌሎችም ለጉዞው የግድ የሚያስፈልገውን ነገር ያሰናዳ ሰው ልክ እንደዘማቹ እንደሚቆጠርና የዘማቾቹን ምንዳ እርሱም እንደሚያገኝ ተናገሩ። የዘማችን ጉዳይ በመልካም ሊሸፍን ሃላፊነት የወሰደ ሰውና እርሱ (ዘማቹ) በራቀበት ወቅት ቤተሰቦቹን ሊንከባከብ የርሱን ቦታ የተተካ ሰውም ልክ እንደዘማች እንደሚቆጠር ተናገሩ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality