Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከሰህል ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:

Available in 44 languages
«ከሰህል ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: «ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። "ጾመኞች የት አሉ?" ይባላል። እነርሱም ይቆማሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። እነርሱ የገቡ ጊዜ ይዘጋል። በርሱ በኩል ማንም አይገባም።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከጀነት በሮች መካከል "የረያን በር" ተብሎ የሚጠራ በር እንዳለና የትንሳኤ ቀን በርሱ በኩል ጾመኞች እንደሚገቡበት ተናገሩ። ከነርሱ ውጪም በርሱ በኩል አንድም ሰው እንደማይገባበት፤ "ጾመኞች የት አሉ?" ተብሎም እንደሚለፈፍ፤ ጾመኞችም ተነስተው እንደሚገቡ፤ በርሱ በኩል ከነርሱ ውጪ ማንም እንደማይገባበት፤ የመጨረሻቸው ሰው ከገባ በኃላ እንደሚዘጋና ከዛ በኋላም በርሱ በኩል ማንም እንደማይገባበት ተናገሩ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality