Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከወሕሺይ ቢን ሐርብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው:

Available in 40 languages
«ከወሕሺይ ቢን ሐርብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «እነርሱ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ እየበላን አንጠግብም።" አሏቸው። እርሳቸውም "ምናልባት ተበታትናችሁ ለየብቻ እየበላችሁ ይሆን?" ብለው ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን" አሉ። እርሳቸውም "ምግብ ስትበሉ ተሰብሰቡ። (አንድ ላይ ብሉ) የአላህንም ስም በምግባቹ ላይ አውሱ። አላህ ምግባችሁን ይባርክላችኋል።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

የተወሰኑ ሶሓቦች ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ በማለት ጠየቁ: "እኛ እንበላለን። ነገር ግን አንጠግብም።" ነቢዩም - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለነርሱ እንዲህ አሏቸው: "ምን አልባት ስትበሉ ተበታትናችሁ ለየብቻ ነው እንዴ የምትበሉት?" እነርሱም: "አዎን" አሉ። እርሳቸውም: "ተሰብሰቡ ሳትበታተኑ ብሉ። ስትበሉ ቢስሚላህ በማለት የአላህን ስም አውሱ። በዛም ይባረክላችኋልም ትጠግባላችሁም።" አሏቸው።

Source
አቡዳውድ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality