Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማ:

Available in 71 languages
«ከዑመር ቢን አልኸጧብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን ነቢይ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰማ: "በአላህ ላይ ትክክለኛውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚለግሰው ለናንተም ሲሳይን ይለግሳቹህ ነበር። (ወፍ) ተርባ ማልዳ ትወጣለች። ሆዷ (በጥጋብ) ሞልቶ ትመለሳለች።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በዱንያዊም በዲናዊም ጉዳይ ጥቅምን በማምጣትና ጉዳትን በመከላከል ረገድ በአላህ ላይ እንድንደገፍ እያነሳሱን ነው። ምክንያቱም ከአላህ በስተቀር የሚሰጥም፣ የሚከለክልም ፣ የሚጎዳም፣ የሚጠቅምም የለምና ነው። ጥቅሞችን የሚያመጡና ጉዳቶችን የሚከላከሉ ሰበቦችን በአላህ ላይ ከእውነተኛ መመካት ጋር እንድንፈፅምም አነሳሱ። ይህንን በማንኛውም ወቅት ከፈፀምን አላህ ወፍን በንጋት የተራበች ሆና ወጥታ ከዚያም በምሽት ሆዷ ሞልቶ በመመለስ እንደሚቀልባት እኛንም ይቀልበን ነበር። ይህም የወፏ ድርጊት ያለመሳነፍና መዳከም ሲሳይን ለመፈለግ የሰራችው የሰበብ አይነት ነው።

Source
ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality