Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:

Available in 70 languages
«ከአቡ መስዑድ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "መንገድ ተቋርጦብኛልና የምጓጓዝበት እንስሳ ይስጡኝ?" አላቸው። እሳቸውም "የለኝም!" አሉት። ሌላ ሰውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ መጓጓዣ የሚሰጠውን እጠቁመዋለሁ!" አለ። የአላህ መልክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ወደ መልካም የጠቆመ ሰው የሰሪውን ምንዳ አምሳያ ይመነዳል።" አሉ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

አንድ ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "እኔ ግመሌ ስለጠፋች የሚያደርሰኝን አንድ መጓጓዣ ይስጡኝ!" አላቸው። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እሳቸው የሚሰጡት ምንም ነገር እንደሌለ ነገሩት። እሳቸው ዘንድ የነበረ አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ የሚሰጠውን ሰው እጠቁመዋለሁ።" አለ። የአላህ መልክተኛም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምፅዋት ፈላጊን ለሚመፀውተው አካል በመጠቆሙ ምክንያት ጠቋሚው ከሚመፀውተው ሰው ጋር በአጅር እንደሚጋራ ተናገሩ።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality