Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 64 languages
«ከኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛውም አይምሮን የሚያደነዝዝና የሚያስወግድ የሚጠጣም ይሁን የሚበላም ይሁን የሚሸተት ወይም ከዚህ ውጪ ያለ ነገር ሁሉ ኸምርና አስካሪ መሆኑን ገለፁ። ሁሉም አስካሪና አይምሮን የሚያስወግድ ነገርም አነሰም በዛም አላህ ከልክሎታል። ከነዚህ የአስካሪ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አይነት የወሰደና በመውሰድ ላይም የዘወተረ እስኪሞት ድረስም ንስሀ ያልገባ ሰውም ጀነት ውስጥ መጠጣትን በመነፈግ የአላህ ቅጣት ይገባዋል።

Source
رواه مسلم وأخرج البخاري الجملة الأخيرة منه
Download image

Saved at original quality