Hadith for the World
ንፅህና (ጦሀራ)

ዉዹእ

8 hadiths

8 hadiths

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ "አንድ ሙስሊም ‐ወይም ሙእሚን‐ የአላህ ባሪያ ውዱእ በሚያደርግበት ጊዜ ፊቱን ሲያጥብ በዓይኑ የተመለከተው ኃጢአት ሁሉ ከፊቱ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እጁን ሲታጠብም እንዲሁ እጆቹ እየዳሰሰች የፈፀመችው ኃጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - እግሩን ሲታጠብም እንዲሁ እግሮቹ ስትራመድ የፈፀመችው ሀጢአት ሁሉ ከውሀው ጋር አብሮ ይፀዳለታል። - ወይም ከመጨረሻው የውሃ ጠብታ ጋር አብሮ ይራገፍለታል። - ልክ እንደዚሁ እያለ ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ ከዉዱኡ እስኪወጣ ድረስ ከኃጢአቱ ይፀዳል።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعًا: «إِذَا لَبِسْتُم، وَإِذَا تَوَضَّأتُم، فَابْدَأُوا بَأَيَامِنُكُم».رواه أبو داود واللفظ له، والترمذي وابن ماجه وأحمد
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ((إن أمتي يُدْعَون يوم القيامة غُرًّا مُحَجَلِّين من آثار الوُضُوء)). فمن اسْتَطَاع منكم أن يُطِيل غُرَّتَه فَليَفعل. وفي لفظ لمسلم: ((رأَيت أبا هريرة يتوضَّأ، فغسل وجهه ويديه حتى كاد يبلغ المنكبين، ثم غسل رجليه حتى رَفَع إلى السَّاقين، ثم قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: إنَّ أمتي يُدْعَون يوم القيامة غُرًّا مُحَجَّلِين من آثار الوُضُوء)) فمن استطاع منكم أن يطيل غُرَّتَه وتَحْجِيلَه فَليَفعَل. وفي لفظ لمسلم: سمعت خليلي صلى الله عليه وسلم يقول: ((تَبْلُغ الحِليَة من المؤمن حيث يبلغ الوُضُوء)).الرواية الأولى: متفق عليه. الرواية الثانية: رواها مسلم. الرواية الثالثة: رواها مسلم
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ዉዱእ በሌለው ጊዜ ዉዱእ እስኪያደርግ ድረስ አላህ ሶላቱን አይቀበለውም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዑሥማን ቢን ዐፋን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ውዱእን አሳምሮ ያደረገ ወንጀሎቹ ከጥፍሮቹ ስር ሳይቀር ከሰውነቱ ባጠቃላይ ይወጣሉ።'"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ከእንቅልፉ የነቃ ጊዜ ሶስት ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ያውጣ፤ ሸይጧን በአፍንጫው ውስጥ ያድራልና።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ለቂጥ ቢን ሰቢራህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንዲህ አሉ: «ወደ አላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከተላኩ የበኒ አልሙንተፊቅ ወይም በበኒ አልሙንተፊቅ ልዑክ ውስጥ ነበርኩ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ስንደርስ በቤታቸው አላገኘናቸውም ነበር። የአማኞች እናትን ዓኢሻን አገኘን። በስጋና ዱቄት የሚሰራ (ኸዚራ) የሚባል ምግብ እንዲሰራልን አዘዘች። ለኛም ተሰራልን። በጎድጓዳ ሳህንም ተምር መጣልን። ከዚያም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጥተው እንዲህ አሉን "የሚቀመስ ነገር አገኛችሁ?" ወይም "የሚቀመስ ነገር ታዘዘላችሁ?" እኛም "አዎ የአላህ መልክተኛ ሆይ!" አልን። እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ የርሳቸው እረኛ ፍየሎቹን ወደ ማደሪያቸው ያስገባ ጀመር። ከርሱ ጋር የምትጮህ ግልገል ነበረች። እርሳቸውም "እከሌ ሆይ! አላራባህምን?" አሉት። እርሱም "ግልገል ናት።" አላቸው። እርሳቸውም "በርሷ ቦታ አንድ ፍየል እረድልና!" አሉት። ቀጥለውም "ለናንተ ብለን የምናርድላችሁ አድርጋችሁ እንዳታስቡ። እኛ መቶ ፍየል አለን። ከመቶ እንዲጨምር ስለማንፈልግ እረኛው አንድ ሲያራባ በርሷ ቦታ አንድ እናርዳለን።" አሉ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ምላሷ ላይ ችግር ያለባት ሚስት አለችኝ። ምን ይሻለኛል?" ብዬ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም "እንደዛ ከሆነ ፍታት" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሷ ከኔ ጋር የቆየ ቁርኝት አላት። ከርሷም ልጆች አሉኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ምከራት! ውስጧ መልካምነት ካለ ትታዘዝሃለች። ሚስትህን የባሪያ አመታት እንዳትመታ።" አሉኝ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለ ዉዱእ ንገሩኝ።" አልኳቸው። እርሳቸውም "ዉዱእን አዳርሰህ አድርግ። በጣቶችህ መካከል ፈልፍል። ፆመኛ እስካልሆንክ ድረስም አፍንጫህ ውስጥ ውሃ ስትከት በደንብ አስገባ።" አሉኝ።»رواه أبو داود والترمذي والنسائي وابن ماجه
አቢ ማሊክ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "ሙስሊም ዘግበውታል።