ዐቂዳ (እምነት)
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው:
Available in 65 languages
«ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ግመል ላይ ሆነው ሙዓዝ ከኋላ ተፈናጦ ሳለ እንዲህ አሉ: 'አንተ ሙዓዝ ቢን ጀበል ሆይ' እርሱም ሶስቴ 'ለጥሪዎት ደጋግሜ አቤት ብያለው በደስታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!' አሁንም 'ሙዓዝ ሆይ!' አሉት: እሱም 'ለጥሪዎት ደጋግሜ አቤት ብያለው በደስታ የአላህ መልክተኛ ሆይ!' አለ። ሶስት ጊዜ ደገሙትና ቀጥለውም ' አንድም በእውነተኛ ልቡ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን የሚመሰክር የለም አላህ በእርሱ ላይ እሳትን እርም ቢያደርግ እንጂ።' አሉ። እርሱም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህንን ለሰዎች ነገሬ ላበስራቸው እንዴ?' አለ። እሳቸውም 'ከነገርካቸውማ (በዚህ ሐዲሥ ላይ) ይደገፋሉ (ይሰንፋሉ)።' አሉ። ሙዓዝ ይህንን ሐዲስ የተናገረው ወንጀል ውስጥ ላለ መውደቅ ብሎ ሊሞት ሲል ነው።"»Meaning translation ·
Saved at original quality








