Hadith for the World
Topic

ዐቂዳ (እምነት)

135 hadiths

135 hadiths

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።' ዑመርም 'በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲከለክሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ራሴ በመናገርም ይሁን የሌላ ሰውን መሀላ ሳስተላልፍ በከለከሉት ምዬ አላውቅም።' አሉ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ አልአሽዐሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "መሳሪያውን በኛ ላይ ያነሳ ከኛ አይደለም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي واقد الحارث بن عوف رضي الله عنه أنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم بينما هو جالس في المسجد، والناس معه، إذ أقبل ثلاثَةُ نَفَرٍ، فأقبل اثنان إلى رسول الله، صلى الله عليه وسلم وذهب واحد، فوقفا على رسول الله صلى الله عليه وسلم ، فأما أحدهما فرأى فُرْجَةً في الْحَلْقَةِ فجلس فيها، وأما الآخر فجلس خلفهم، وأما الثالث فأدْبَر ذاهبٍا، فلما فرغ رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «ألا أُخْبِرُكُم عن النَّفَرِ الثلاثة: أما أحدهم فأَوَى إلى الله فآوَاهُ الله إليه، وأما الآخر فاسْتَحْيا فاسْتَحْيَا الله منه، وأما الآخر، فأعْرَضَ، فأعرضَ اللهُ عنه».متفق عليه
ከዑመር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና - እንደተላለፈው: "ዑመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ (ሐጀሩል አስወድ) መጣና ሳመው። እንዲህም አለ: እኔ የማትጎዳና የማትጠቅም ድንጋይ መሆንህን አውቃለሁ። እኔ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሲስሙህ ባላይህ ኖሮ አልስምህም ነበር።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس بن مالك رضي الله عنه أنَّ رَجُلاً كَانَ عِند النَبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَمَرَّ رَجُلٌ بِهِ، فقال: يا رسول الله، أنِّي لَأُحِبُّ هَذَا، فَقَال لَهُ النَبِيُّ صلى الله عليه وسلم : «أَأَعْلَمْتَهُ؟» قال: لا. قال: «أَعْلِمْهُ»، فَلَحِقَهُ، فقال: إِنِّي أُحِبُّك فِي الله، فقال: أّحَبَّك الَّذِي أَحْبَبْتَنِي لَهُ.رواه أبو داود والنسائي في الكبرى وأحمد
عن يزيد بن حيان قال: انطلقت أنا وحُصين بن سَبْرَة وعمرو بن مسلم إلى زيد بن أرقم رضي الله عنه فلما جلسنا إليه قال له حصين: لقد لقيتَ يا زيد خيرًا كثيرًا، رأيتَ رسول الله صلى الله عليه وسلم وسمعتَ حديثه، وغزوتَ معه، وصليتَ خلفه: لقد لقيت يا زيد خيرًا كثيرًا، حدثنا يا زيد ما سمعت من رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: يا ابن أخي، والله لقد كَبِرَتْ سني، وقَدُمَ عهدي، ونسيتُ بعض الذي كنت أَعِي من رسول الله صلى الله عليه وسلم فما حدثتكم فاقبلوا، وما لا فلا تُكَلِّفُونِيهِ. ثم قال: قام رسول الله صلى الله عليه وسلم يومًا فينا خطيبًا بماء يُدعى خُمًّا بين مكة والمدينة، فحمد الله، وأثنى عليه، ووعظ وذكَّر، ثم قال: «أما بعد، ألا أيها الناس، فإنما أنا بشر يُوشِكُ أن يأتي رسول ربي فأُجِيبَ، وأنا تاركٌ فيكم ثَقَلَيْنِ: أولهما كتاب الله، فيه الهدى والنور، فخذوا بكتاب الله، واستمسكوا به»، فحَثَّ على كتاب الله، ورغَّبَ فيه، ثم قال: «وأهل بيتي أُذَكِّرُكُمُ اللهَ في أهل بيتي، أُذَكِّرُكُمُ اللهَ في أهل بيتي» فقال له حصين: ومن أهل بيته يا زيد، أليس نساؤه من أهل بيته؟ قال: نساؤه من أهل بيته، ولكن أهل بيته من حُرِمَ الصدقةَ بعده، قال: ومن هم؟ قال: هم آل علي، وآل عقيل، وآل جعفر، وآل عباس. قال: كل هؤلاء حُرِمَ الصدقةَ؟ قال: نعم. وفي رواية: «ألا وإني تاركٌ فيكم ثَقَلَيْنِ: أحدهما كتاب الله وهو حبل الله، من اتبعه كان على الهدى، ومن تركه كان على ضلالة».رواه مسلم
ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት። እርሱም "እኔ አላህና መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደዴ ውጭ ምንም ነገር አላዘጋጀሁም።" አለ። እርሳቸውም "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" አሉት። አነስም እንዲህ አሉ፦ "በዚህ "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" በሚለው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር እንደተደሰትነው በምንም አልተደሰትንም።" ቀጥሎም (አነስ) እንዲህ አሉ: "እኔ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን እወዳለሁ። እነርሱ የሰሩትን አምሳያ ባልሰራ እንኳ እነርሱን በመውደዴ ከነርሱ ጋር መሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن مرداس الأسلمي رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ -صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ-: «يذهب الصالحون الأول فالأول، ويبقى حُثَالَةٌ كَحُثَالَةِ الشعير أو التمر لا يُبَالِيهُم الله بَالَةً».رواه البخاري
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው በጓደኛው ሃይማኖት ላይ ነው። አንዳችሁ የሚጎዳኘውን ሰው ይመልከት።"አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሀዲ ሆኖ የሚያመሽበት፤ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሀዲ ሆኖ የሚያነጋበት፤ እምነቱንም በአለማዊ ሸቀጥ እስከመሸጥ የሚያደርሱ የድቅድቅ ጨለማ ቁራጭ የመሰሉ ፈተናዎች ከመምጣታቸው በፊት በመልካም ስራ ተቻኮሉ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عائشة رضي الله عنها قالت: «ما غِرْتُ على أحد من نساء النبي صلى الله عليه وسلم ما غِرْتُ على خديجة رضي الله عنها ، وما رأيتها قط، ولكن كان يُكثر ذِكْرَها، وربما ذبح الشَّاةَ، ثم يُقطعها أَعْضَاءً، ثم يَبْعَثُهَا في صَدَائِقِ خديجة، فربما قلت له: كأن لم يكن في الدنيا إلا خديجة! فيقول: «إنها كانت وكانت وكان لي منها وَلَدٌ». وفي رواية: وإن كان لَيَذْبَحُ الشَّاءَ، فيُهدي في خَلَائِلِهَا منها ما يَسَعُهُنَّ. وفي رواية: كان إذا ذَبَحَ الشَّاةَ، يقول: «أرسلوا بها إلى أصدقاء خديجة». وفي رواية: قالت: اسْتَأْذَنَتْ هالة بنت خويلد أخت خديجة على رسول الله صلى الله عليه وسلم فعرف استئذان خديجة، فارْتَاحَ لذلك، فقال: «اللهم هالة بنت خويلد».الرواية الأولى: متفق عليها. الرواية الثانية: متفق عليها. الرواية الثالثة: متفق عليها. الرواية الرابعة: متفق عليها
ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ እንዲህ አያሉ ደንግጠው ገቡ: "ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።" አሉና በአውራ ጣታቸውና በጠቋሚ ጣታቸው ክብ አደረጉ። ዘይነብ ቢንት ጀሕሽም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በመካከላችን ደጋጎች እያሉ እንጠፋለን?" አለች። እርሳቸውም "አዎን ፀያፍ የበዛ ጊዜ" አሏት።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር: «አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ያ የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ኡመት ውስጥ አንድም አይሁድ ይሁን ክርስቲያን ስለኔ ሰምቶ ከዚያም በዛ በተላኩበት ሳያምን የሚሞት የለም። ከእሳት ጓዶች መካከል ቢሆን እንጂ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: «الإيمانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أو بِضْعٌ وسِتُّونَ شُعْبَةً: فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ: لا إله إلا الله، وَأَدْنَاهَا إِمَاطَةُ الأَذَى عَنِ الطَّرِيقِ، وَالحَيَاءُ شُعْبَةٌ مِنَ الإِيمَانِ».متفق عليه
عن معاذ بن أنس رضي الله عنه مرفوعًا: «مَن كَظَمَ غَيظًا، وَهُو قادر على أن يُنفِذَه، دَعَاه الله سبحانه وتعالى على رؤوس الخَلاَئِق يوم القيامة حتَّى يُخَيِّره من الحُور العَين مَا شَاء».رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"አሕመድ ዘግበውታል።
عن أنس بن مالك رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه قال: "إن عِظَمَ الجزاءِ مع عِظَمِ البلاءِ، وإن الله تعالى إذا أحب قوما ابتلاهم، فمن رَضِيَ فله الرِضا، ومن سَخِطَ فله السُّخْطُ".رواه الترمذي وابن ماجه
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አላህ ይቀናል። አማኝ የሆነ ሰውም ይቀናል። የአላህ መቅናት ሰውዬው አላህ በሱ ላይ ክልክል ያደረገበትን ሲዳፈር ነው።›"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ ተገኝተው ወደማይሰግዱ ሰዎች ቤት የታሰረ እንጨት ከያዙ ወንዶች ጋር በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።