Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

Available in 70 languages
«ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ ማለቱን እየነገሩን ነው፡- አጋርን ከመፈለግ ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃው አሏህ ነው። እርሱም ከምንም የተብቃቃ ራሱን የቻለ ነው። አንድ ሰው መልካም ነገርን ሲያደርግ ለአላህም ለሌሎችም ብሎ ቢያደርገው አላህ ይህንን ስራውን ይተውለታል፤ አይቀበለውም፤ ወደራሱ ይመልስለታል። ስለዚህም ጥራት የተገባው አሏህ ጥርት ባለ መልኩ ለርሱ ተብሎ የተሰራውን መልካም ስራ ካልሆነ በቀር ሌላን ስራ ስለማይቀበል ኢኽላስን ለርሱ ማድረግ ግዴታ ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality