Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 62 languages
«ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው። የትንሳኤ ቀን ሰዎች በስራዎቻቸው የተመነዱ ጊዜ ለነርሱ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ይላቸዋል፦ 'እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ?' "»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ላይ እጅግ የሚፈሩት ነገር ትንሹን ሺርክ እንደሆነ እሱም ይዩልኝ እንደሆነ ተናገሩ። ይሀውም ለሰዎች ብሎ መስራቱ ነው። ቀጥለውም ለይዩልኝ የሚሰሩ ሰዎች የትንሳኤ ቀን የሚጠብቃቸውን ቅጣት ተናገሩ። ለነርሱ: "እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ? ለዚህ ስራችሁ ለናንተ መመንዳትና አጅር መስጠት ይችላሉን?" እንደሚባሉም ተናገሩ።

Source
አሕመድ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality