Hadith for the World
ስሞችና ህግጋት

ማጋራት (ሺርክ)

4 hadiths

4 hadiths

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"አሕመድ ዘግበውታል።
ከመሕሙድ ቢን ለቢድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በናንተ ላይ ከምፈራው ነገር እጅግ አስፈሪው ትንሹ ሺርክ ነው።" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ትንሹ ሺርክ ምንድነው?" ብለው ጠየቁ። እሳቸውም "ይዩልኝ ነው። የትንሳኤ ቀን ሰዎች በስራዎቻቸው የተመነዱ ጊዜ ለነርሱ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ይላቸዋል፦ 'እነርሱ ዘንድ ምንዳን ታገኙ እንደሁ እስኪ በዱንያ ውስጥ ለይዩልኝ ወደምትሰሩላቸው ሂዱና ተመልከቱ?' "አሕመድ ዘግበውታል።
عن عبد الله بن عمرو بن العاص - رضي الله عنه- مرفوعاً: "مَن ردته الطِّيَرَة عن حاجته فقد أشرك، قالوا: فما كفارة ذلك؟ قال: أن تقول: اللهم لا خير إلا خيرك، ولا طَيْرَ إِلَّا طَيْرُكَ ولا إله غيرك".رواه أحمد
ከቡረይዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "(በአማና) በአደራ የማለ ሰው ከኛ አይደለም።"አቡዳውድና አሕመድ ዘግበውታል።