AM
ስሞችና ህግጋት
ኢስላም
3 hadiths
ኢስላም
3
ኢስላምን የሚያፈርሱ ነገሮች
1
የጃሂሊያ ጉዳዮች
1
የኢማን መጨመርና መቀነስ
5
የኢማን ቅርንጫፍ
3
ክህደት (ኩፍር)
2
ማጋራት (ሺርክ)
4
ንፍቅና (ኒፋቅ)
1
አመፀኝነት (ፊስቅ)
1
ቢድዓ
2
3 hadiths
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካ መስጠት፣ በተከበረው የአሏህ ቤት ሐጅ ማድረግ እና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በጃሂሊያ (በድንቁርናው)ዘመን ዝምድናን የሚቀጥልና ሚስኪኖችን የሚመግብ ነበር። ይህ ይጠቅመዋልን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ወንጀሎቼን ማረኝ" ብሎ ስለማያውቅ አይጠቅመውም።" አሉ።
ሙስሊም ዘግበውታል።