Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦

Available in 71 languages
«የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ኢብኑ ጁድዓን በጃሂሊያ (በድንቁርናው)ዘመን ዝምድናን የሚቀጥልና ሚስኪኖችን የሚመግብ ነበር። ይህ ይጠቅመዋልን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ወንጀሎቼን ማረኝ" ብሎ ስለማያውቅ አይጠቅመውም።" አሉ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከእስልምና በፊት የቁረይሽ ሹማምንቶች መካከል ስለነበረው ዐብደላህ ቢን ጁድዓን ተናገሩ። ከመልካም ሥራዎቹ መካከልም፦ ዝምድናውን የሚቀጥል፣ ለነሱ መልካም የሚሰራ፣ ሚስኪኖችን የሚመግብና ሌሎችም እስልምና እንዲተገበር ያነሳሳቸውን መልካም ስራዎች የሚሰራ ነበር። እነዚህ ተግባሮቹ ግን በአላህ በመካዱና አንድ ቀንም "ጌታዬ ሆይ! የምንዳው ቀን ለኔ ወንጀሎቼን ማረኝ" ባለማለቱ ምክንያት ለመጪው ዓለም አትጠቅመውም።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality