Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦

Available in 62 languages
«ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላትን ከመተው አስጠነቀቁ። በሰውዬውና ሺርክና ክህደት ላይ በመውደቅ መካከል ያለው ግርዶ ሶላትን መተው እንደሆነም ተናገሩ። ሶላት ከኢስላም ማእዘናቶች መካከል ሁለተኛው ማእዘን ነው፣ ሶላት በኢስላም ትልቅ ጉዳይ ነው። ግዴታነቱን አስተባብሎ የተወ ሰው በሁሉም ዑለማእ (የኢስላም ሊቃውንት) ስምምነት መሰረት ክዷል። በስንፍናና ድክመት ምክንያት ሙሉ ለሙሉ የተወም እንደዚሁ ከሀዲ ነው። በዚህ ዙሪያ የሶሐቦች ሙሉ ስምምነት እንዳለም ተሰምቷል። አንዳንዴ የሚተው አንዳንዴ የሚሰግድ ከሆነ ደግሞ ለዚህ ከባድ ዛቻ የተጋረጠ ይሆናል።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality