Hadith for the World
ሶላት

የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ

5 hadiths

5 hadiths

ዐምር ቢን ሹዐይብ ከአባቱ፣ አባቱም ከአያቱ እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!"አቡዳውድ ዘግበውታል።
ከቡረይዳህ ቢን ሑሰይብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የዐስርን ሰላት ወቅቱ እንደገባ ቶሎ ስገዱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋልና: ' የዐስርን ሶላት የተወ ሰው በርግጥም ስራው ተበላሸ።'"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካ መስጠት፣ በተከበረው የአሏህ ቤት ሐጅ ማድረግ እና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ሶላትን የረሳ ሰው ባስታወሰው ጊዜ ይስገድ። ከዚህ በቀር ማካካሻ የለውም። {ሶላትንም (በርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።} [ጣሀ:14]ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'"ሙስሊም ዘግበውታል።