Hadith for the World
ሶላት

የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት

7 hadiths

7 hadiths

عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعًا: «صلاة الرجل في جماعة تَضعُفُ على صلاته في بيته وفِي سُوقِه خمسا وعشرين ضِعفًا، وذلك: أَنَّه إِذَا تَوَضَّأ، فَأَحسَن الوُضُوء، ثمَّ خرج إلى المسجد لاَ يُخرِجُهُ إلاَّ الصلاة؛ لَم يَخْطُ خُطوَةً إِلاَّ رُفِعَت له بِها درجة، وَحُطَّ عَنهُ بها خطيئة، فإذا صلَّى لم تزل الملائكة تُصَلِّي عليه، ما دام في مُصَلاَّه: اللهُمَّ صَلِّ عليه، اللهم اغفِر له، اللهم ارْحَمه، ولا يزال في صلاة ما انتظر الصلاة».متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች። ይህም አንዳቸው ዉዱእ ሲያደርግ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከሶላት በስተቀር ሳያንቀሳቅሰው ከሶላትም በስተቀር ሌላን ሳይፈልግ ወደ መስጅድ ከመጣ መስጂድ እስኪገባ ድረስ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ልክ ለርሱ ደረጃው ከፍ ይደረግለታል፤ ወንጀሉም ከርሱ ላይ በሷው ይራገፍለታል። መስጂድ የገባ ገዜም በሶላቷ ምክንያት እስከተጠመደ ድረስ ሶላት ውስጥ ነው። አንዳችሁ በሰገደበት ስፍራ ላይ እስከዘወተረ ድረስም ሰዎችን እስካላወከና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላእክቶች በርሱ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ። 'አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው' ይላሉም።'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።" ቀጥሎም አቡ ሁረይራ እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {የጎህ ሶላት ( መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78]»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰውዬ መጣ። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም።' በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በቤቱ መስገድን እንዲያገሩለት ጠየቀ። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜ ጠሩትና 'የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الرحمن بن أبي عمرة قال: دخل عثمان بن عفان المسجد بعد صلاة المغرب، فقعد وحده، فقعدتُ إليه فقال: يا ابن أخي، سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «من صلى العشاء في جماعة فكأنما قام نصف الليل، ومن صلى الصبح في جماعة فكأنما صلى الليل كله».رواه مسلم
عن أبي موسى قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم: «أعظم الناس أجرًا في الصلاة أبعدهم فأبعدهم ممشى، والذي ينتظر الصلاة حتى يصليها مع الإمام أعظم أجرًا من الذي يصلي ثم ينام».متفق عليه