ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
Available in 60 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች። ይህም አንዳቸው ዉዱእ ሲያደርግ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከሶላት በስተቀር ሳያንቀሳቅሰው ከሶላትም በስተቀር ሌላን ሳይፈልግ ወደ መስጅድ ከመጣ መስጂድ እስኪገባ ድረስ በሚራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ልክ ለርሱ ደረጃው ከፍ ይደረግለታል፤ ወንጀሉም ከርሱ ላይ በሷው ይራገፍለታል። መስጂድ የገባ ገዜም በሶላቷ ምክንያት እስከተጠመደ ድረስ ሶላት ውስጥ ነው። አንዳችሁ በሰገደበት ስፍራ ላይ እስከዘወተረ ድረስም ሰዎችን እስካላወከና ዉዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላእክቶች በርሱ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ። 'አላህ ሆይ እዘንለት፣ አላህ ሆይ ማረው፣ አላህ ሆይ ፀፀቱን ተቀበለው' ይላሉም።'"»Meaning translation ·
Saved at original quality








