Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ።

Available in 62 languages
«ከአቡል ሐውራእ አስሰዕዲይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: ለሐሰን ቢን ዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ምን ሸምድደሃል? አልኩት። እርሱም: "ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ሸምድጃለሁ አለኝ። ‹የሚያጠራጥርህን ነገር ተውና ወደ ማያጠራጥርህ ሂድ! እውነት እርጋታን የተላበሰ ነው። ውሸት ደሞ ጥርጣሬን የተላበሰ ነው።›"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ክልክል ነው ወይስ አይደለም፣ ሐላል ነው ወይስ ሐራም ነው እያልክ የምትጠራጠርበት ንግግርና ተግባር በመተው መልካምነቱንና ፍቁድነቱን እርግጠኛ ወደሆንክበትና ወዳልተጠራጠርክበት መሄድን አዘዙ። ቀልብ እርግጠኛ በሆነበት ነገር ላይ ይረጋል። አጠራጣሪ በሆነ ነገር ደግሞ ይወዛገባል።

Source
رواه الترمذي والنسائي وأحمد
Download image

Saved at original quality