Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦

Available in 42 languages
«ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።" ቀጥሎም አቡ ሁረይራ እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {የጎህ ሶላት ( መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78]»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰውዬው ከኢማም ጋር በህብረት የሚሰግደው ሶላት ምንዳና አጅሩ ቤቱ ወይም ሱቁ ውስጥ ብቻውን ከሚሰግደው ሃያ አምስት ሶላት እንደሚበልጥ ገለፁ። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የምሽትና የቀን መልዐክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት እንደሚሰባሰቡ አወሱ። ቀጥሎም አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይህንን ለማመሳከር እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ: {የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78] ማለትም: የፈጅር ሶላት የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች የሚገኙበት ነው ማለት ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality