Hadith for the World
ሶላት

የሶላት ትሩፋት

10 hadiths

10 hadiths

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ ተገኝተው ወደማይሰግዱ ሰዎች ቤት የታሰረ እንጨት ከያዙ ወንዶች ጋር በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር፡ "ትላልቅ ወንጀሎችን ከተጠነቀቀ አምስቱ ሶላቶች፣ ከጁሙዐ እስከ ጁሙዐ፣ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመካከላቸው የተሰሩትን ወንጀሎች ያስሰርዛሉ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ ነፃ ያወጡት ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ምክንያት ጀነት እንድገባ የሚያደርገኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ፦ "'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?' ሶሐቦችም 'ከእድፉ አንዳችም አያስቀርም።' አሉ። እርሳቸውም 'ይህ የአምስቱ ሶላቶች ምሳሌ ነው። አላህ በሶላት ወንጀሎችን ያብሳል።' አሉ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጁንዱብ ቢን ዐብደላህ አልቀስሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው። ከናንተ አንዳችሁ በአላህ ጥበቃ ስር ያለውን ሰው በምንም መንገድ አይጉዳ። ያንን የሠራ ሰው የአላህ ቁጣ በእርግጥ ይይዘዋል ከዚያም በአፍጢሙ በጀሀነም እሳት ውስጥ ይደፋዋል።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ዙሀይር ዑማረህ ቢን ሩአይበህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ፀሐይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት የሰገደ አንድም ሰው እሳት አይገባም።"»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜ ልኩን ነው።'"ሙስሊም ዘግበውታል።
አቢ ማሊክ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ربيعة بن كعب الأسلمي قال: كنتُ أبيتُ مع رسول الله صلى الله عليه وسلم فأتيتُه بوَضوئه وحاجته فقال لي: «سل» فقلت: أسألك مرافقتك في الجنة. قال: «أو غير ذلك؟» قلت: هو ذاك. قال: «فأعني على نفسك بكثرة السجود».رواه مسلم
عن عائشة عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «ما من ميت تصلي عليه أُمَّةٌ من المسلمين يبلغون مائة، كلهم يشفعون له، إلا شفعوا فيه».رواه مسلم