Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከጁንዱብ ቢን ዐብደላህ አልቀስሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ:

Available in 70 languages
«ከጁንዱብ ቢን ዐብደላህ አልቀስሪይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "የሱብሒን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ከለላ ስር ነው። ከናንተ አንዳችሁ በአላህ ጥበቃ ስር ያለውን ሰው በምንም መንገድ አይጉዳ። ያንን የሠራ ሰው የአላህ ቁጣ በእርግጥ ይይዘዋል ከዚያም በአፍጢሙ በጀሀነም እሳት ውስጥ ይደፋዋል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት የሰገደ ሰው በአላህ ጥበቃና ከለላ ስር ስላለ እንደሚከላከልለትና እንደሚረዳው ተናገሩ። ከዚያም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የፈጅርን ሶላት በመተው ወይም ሰጋጁን በመተናኮልና ሰጋጁ ላይ ወሰን በማለፍ ይህንን ከለላ ከማፍረስ አስጠነቀቁ። ይህንን የፈፀመም ይህንን ጥበቃ ስለጣሰ ለብርቱ ዛቻ የተጋለጠ ይሆናል። የአላህን ሀቅ ወሰን ስላለፈም በአላህ ይፈለጋል። አላህም የሚፈልገውን ያገኘዋል፤ ከዚያም በአፍጢሙ እሳት ውስጥ ይደፋዋል።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality