Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው:

Available in 55 languages
«ከዐብደላህ ቢን ሰላም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መዲና የገቡ ጊዜ ሰዎች ወደርሳቸው በፍጥነት ሄዱ። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ፤ የአላህ መልክተኛ ገቡ ‐ ሶስት ጊዜ ‐ እየተባለ ተወራ። ለመመልከትም ከሆኑ ሰዎች ጋር መጣሁ። ፊታቸውን የተመለከትኩኝ ጊዜ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቅኩ። መጀመሪያ ሲናገሩ የሰማሁት ነገር እንዲህ ሲሉ ነው: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መዲና መጥተው ሰዎች የተመለከቷቸው ጊዜ ወደርሳቸው አቅጣጫ በፍጥነት ሄዱ። ዐብደላህ ቢን ሰላምም ያኔ አይሁድ ነበርና ወደርሳቸው ከመጡት መካከል አንዱ ነው። እርሳቸውን ሲያይም በርሳቸው ላይ ብርሃንን፣ ውበትንና እውነተኛ ግርማን በማየቱ ፊታቸው የውሸታም ፊት እንዳልሆነ አወቀ። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንደበት ለመጀመሪያ የሰማውም ነገር ሰዎችን ጀነት ለመግባት ሰበብ የሚሆናቸውን ተግባራት ላይ ማነሳሳታቸውን ነው። መጀመሪያ: ባወቅከውም ይሁን ባላወቅከውም ሰው ላይ ሰላምታን ማሰራጨትና ማብዛት ነው። ሁለተኛ: ምግብን በሶደቃ፣ በስጦታና በእንግድነት መልክ ማብላት ነው። ሶስተኛ: በአባት ወይም በእናት በኩል ቅርበትና ዝምድና ከምትተሳሰርው አካል ጋር ዝምድናን መቀጠል ነው። አራተኛ: ሰዎች በተኙበት ለሱና (ግዴታ ላልሆነ) ሶላት ሌሊት መቆም ነው።

Source
ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality