Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

Available in 54 languages
«ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከእንግዳ ሴቶች ጋር ከመቀላቀል እንዲህ በማለት አስጠነቀቁ "በሴቶች ላይ ከመግባትና ሴቶችም እናንተ ዘንድ እንዳይገቡ ነፍሳችሁን ጠብቁ!" አንድ የአንሷር ሰውዬም እንዲህ አለ: እስኪ ንገሩኝ የባል ወንድም፣ የወንድሙ ልጅ፣ አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ የእህቱ ልጅና የመሳሰሉት ባታገባ ኖሮ ልታገባቸው የሚፈቀዱላት የባል ቅርብ ዘመዶች ቢገቡስ ይፈቀዳልን? ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ በማለት መለሱ: "ሞትን እንደምትጠነቀቁት እርሱንም ተጠንቀቁት! ከባል ዘመዶች ጋር ገለል ብሎ ማሳለፍ ለሃይማኖት ፈተናና ጥፋት የሚመራ ነው። ከአባቱና ከልጆቹ ውጪ ያሉ የባል ቅርብ ዘመዶችን መከልከል ከሌላው ባዳ ወንድ የበለጠ የተገባ ነው። ይህም ከሌላ ባዳ ጋር ለብቻ ከምታሳልፍበት ጊዜ ይልቅ ከባል ቅርብ ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ እድሉ የበዛ ስለሆነ ከሌላው በበለጠ ከርሱ ጋር መጥፎ ነገር መከሰቱ ስለሚገመትና ያለምንም አውጋዥ ወደ ሴቷ መድረስና ከርሷ ጋር ለብቻ ማሳለፍ ስለሚችል ፈተና የመከሰት እድሉም የሚመች ነው። በተለምዶ የባል ወንድም የወንድሙ ሚስት ብቻዋን እያለች መግባት ቸል የሚባል ጉዳይ ስለሆነ ፈተና መከሰቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ከባዳ ወንድ ጋር ለብቻ ማሳለፍማ የሚጠነቀቁት ጉዳይ ነው። ከርሱ በተቃራኒ ከባል ዘመድ ጋር ለብቻ የማሳለፍ አፀያፊነትና የሚያስከትለው ችግር ግን ከሞት ጋር ይመሳሰላል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality