Hadith for the World
የቤተሰብ ፊቂህ

የሴቶች ህግጋት

10 hadiths

10 hadiths

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ! የበኒ ኢስራኢሎች የመጀመሪያ ፈተና የተከሰተው በሴቶች ነበርና።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንድ አማኝ ወንድ አንዲትን አማኝ እንስት አይጥላ። ከርሷ አንድ ባህሪዋን ቢጠላ እንኳ ሌላ የሚወደው ባህሪ አላትና።" ወይም "ከርሱ ውጪ ያለን ባህሪ… " ብለዋል።ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي شريح خويلد بن عمرو الخزاعي و أبي هريرة رضي الله عنهما عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «اللَّهُمَّ إِنِّي أُحَرِّجُ حَقَّ الضَعِيفَين: اليَتِيم والمَرْأَة».حديث أبي شريح رواه النسائي. وحديث أبي هريرة رواه ابن ماجه وأحمد
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ መጣቀሚያ ናት። ከዱንያ መጣቀሚያዎች ምርጡ መልካም ሚስት ናት።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዑቅበህ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሴቶች ጋር ከመግባት ተጠንቀቁ!" አንድ ከአንሷር የሆነ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ስለባል ቅርብ ዘመዶች ንገሩኝ እስኪ?" አለ። እርሳቸውም "የባል ቅርብ ዘመድማ ሞት ነው።" አሉ።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአስወድ ቢን የዚድ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ዓኢሻን ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቤት ውስጥ ስለሚሰሩት ስራ ጠየቅኳት? እርሷም: "የሚያሳልፉት ቤተሰባቸውን በማገልገል ነው። ሶላት ሲደርስ ሶላት ለመስገድ ይወጣሉ።" አለች።»ቡኻሪ ዘግበውታል።
عن أبي سعيد الخُدْرِي رضي الله عنه قال: جاءت امرأة إلى رسول الله صلى الله عليه وسلم فقالت: يا رسول الله، ذهب الرجال بِحَدِيثِكَ، فاجْعَل لنَا من نَفْسِك يومًا نَأتِيكَ فيه تُعَلِّمُنَا مما عَلَّمَكَ الله، قال: «اجْتَمِعْنَ يَوَم كَذَا وكَذَا» فَاجْتَمَعْنَ، فأتَاهُنَّ النبي صلى الله عليه وسلم فَعَلَّمَهُنَّ مما عَلَّمَهُ الله، ثم قال: «ما مِنْكُنَّ من امرأة تُقَدِّمُ ثَلاَثَة من الولد إلا كانوا حِجَابًا من النَّارِ» فقالت امرأة: واثنين؟ فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «واثنين».متفق عليه
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዒድ አልአድሓ ወይም በዒድ አልፈጥር ወደ መስገጃ ስፍራ ሲሄዱ በሴቶች በኩል አለፉና እንዲህም አሉ: "እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ። ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዲናችንና አይምሯችን መጉደል ምንድን ነው?" አሉ። እርሳቸውም "የአንድ ሴት ልጅ ምስክር እንደ ግማሽ የወንድ ምስክር አይደለም የሚቆጠረው?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የአይምሮዋ መጉደሉ ነው። የወር አበባ ባየች ጊዜ አትሰግድምም አትጾምም አይደል?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የዲናቸው መጉደሉ ነው።" አሉ።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ابن عباس رضي الله عنهما أنه سمع النبي صلى الله عليه وسلم يقول: «لا يَخْلُوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ، ولا تسافِرَنَّ امرأةٌ إلا ومعها محرمٌ»، فقام رجل فقال: يا رسول الله، ‌اكتتبت في غزوة كذا وكذا، وخرجت امرأتي حاجة، قال: «اذهب فحج مع امرأتك».متفق عليه