Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:

Available in 39 languages
«ከኢብኑ ዐባስ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ኢብኑ ዓባስ ለዐጧእ ቢን አቢ ረባሕ እንዲህ አሉ:«ከጀነት ሰዎች መካከል የሆነች ሴት አላሳይህምን?" እኔም "እንዴታ!" አልኩኝ። እርሳቸውም እንዲህ አሉኝ: "ይህቺ ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: ‹እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝና እገላለጣለሁ። እንዲፈውሰኝ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም: ‹ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለሽ። ከፈለግሽ ደሞ ጤናን እንዲለግስሽ አላህን እለምንልሻለሁኝ።› አሏት። እርሷም ‹እታገሳለሁ።› ብላ እንዲህም አለች: ‹እኔ እገላለጣለሁኝ። እንዳልገላለጥ አላህን ለምኑልኝ።› እርሳቸውም ዱዓ አደረጉላት።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ኢብኑ ዐባስ (አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና) ለዐጧእ ቢን አቢረባሕ እንዲህ አሉ: "የጀነት ነዋሪ የሆነችን ሴት አላሳይህምን?" ዐጧእም "እንዴታ!" አለ። ኢብኑ ዐባስም እንዲህ አሉ: "ይህቺ ሐበሻዊት ጥቁር ሴት ናት። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣችና እንዲህ አለች: "የሚጥል በሽታ ስላለብኝ ይጥለኝና እገላለጣለሁኝ። ታዲያ እኔ ሳላውቀው ከሰውነቴ የተወሰነው ክፍል ይገለጣል። አላህ ጤናን እንዲለግሰኝ ለምኑልኝ።" እርሳቸውም እንዲህ አሏት: "ከፈለግሽ ታግሰሽ ላንቺ ጀነት አለልሽ። ከፈለግሽ ደግሞ አላህ ጤናን እንዲሰጥሽ እለምንልሻለሁኝ።" እርሷም እንዲህ አለች: "እንዲህ ከሆነ እታገሳለሁኝ። አክላም "ስወድቅ እንዳልገላለጥ ግን አላህን ይለምኑልኝ።" አለች። እርሳቸውም አላህን ለመኑላት።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality