Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር:

Available in 41 languages
«ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር: «አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም የሆነ ሰው ለሙስሊም ወንድሙ ከሩቅ ‐ ዱዓ የሚደረግለት ሰው በሌለበት ‐ የሚያደርገው ዱዓ ተቀባይነት እንዳለው ተናገሩ። ይህም የኢኽላስ ጥግ የደረሰ ዱዓ ስለሆነ ነው። ዱዓ አድራጊው ጭንቅላት ዘንድም የተወከለ መልአክ እንዳለና ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገ ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክ "አሚን ላንተም ዱዓ ያደረግከውን አምሳያ ይስጥህ።" እንደሚልም ተናገሩ።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality