Hadith for the World
ደረጃ ያላቸው ስራዎች

የዱዓእ ትሩፋቶች

5 hadiths

5 hadiths

ከኡሙ ደርዳ እና ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ይሉ ነበር: «አንድ ሙስሊም ሰው ለወንድሙ ከሩቅ (በሌለበት) የሚያደርግለት ዱዓ ተቀባይነት አለው። ከጭንቅላቱ በላይ የተወከለ መልአክ አለ። ለወንድሙ መልካም ነገርን ዱዓ ባደረገለት ቁጥር ለዚህ ጉዳይ የተወከለው መልአክም "አሚን ላንተም ተመሳሳዩ አለህ።" ይለዋል።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: 'ዱዓእ እሱ አምልኮ ነው።' ከዚያም {ጌታችሁም አለ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።"} [ጋፊር: 60] የሚለውን አነበቡ።"አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ከዱዓእ የበለጠ አላህ ዘንድ የተከበረ አንዳችም ነገር የለም።"ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة أن رسول الله صلى الله عليه وسلم ذكر يوم الجمعة، فقال: «فيه ساعة، لا يوافقها عبدٌ مسلمٌ، وهو قائم يصلي، يسأل الله تعالى شيئًا، إلا أعطاه إياه» وأشار بيده يقللها.متفق عليه