Hadith for the World
ደረጃ ያላቸው ስራዎች

የዚክር ትሩፋቶች

10 hadiths

10 hadiths

ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣ ለናንተ ወርቅና ብር ከመመፅወት የሚበልጥላችሁን ስራ፣ ጠላቶቻችሁን ተገናኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱበት አንገታችሁን ከሚመቱበት ስራችሁም በላጩ የሆነውን ስራ አልነግራችሁምን?" ሶሐቦችም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "አላህን ማውሳት ነው።" አሉ።»ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመካ መንገድ ላይ እየተጓዙ ሳለ ጁምዳን በሚባል ተራራ ላይ ሲያልፉ እንዲህ አሉ: "ይህ ጁምዳን ነው ተጓዙ! ሙፈሪዶች ቀደሙ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሙፈሪዶች እነማን ናቸው?" አሉ። እርሳቸውም "አላህን በብዛት የሚያወሱ ወንዶችና ሴቶች ናቸው።" አሉ።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአልአገርሪ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች መካከል አንዱ ነበር። እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።)"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከላቀውና ከተከበረው ጌታቸው ባስተላለፉት (ሐዲሥ) እንዲህ አሉ "አንድ ባሪያ አንድን ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ! " የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ!" ከዚያም አሁንም ደግሞ ወንጀል ሰራና እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ!" የጠራውና ከፍ ያለውም እንዲህ አለ "ባሪያዬ ወንጀልን ሰርቶ ወንጀልን የሚምርና በወንጀሉም የሚይዘው ጌታ እንዳለው አወቀ! የፈለግከውን ስራ በርግጥ ላንተ ምሬሃለሁ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي ذر الغفاري رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «ألاَ أُخْبِرُكَ بِأَحَبِّ الكَلاَمِ إِلَى اللهِ؟ إنَّ أَحَبَّ الكلام إِلى الله: سبحان اللهِ وبحمدِهِ».رواه مسلم
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: «والذي نفسي بيده، لو لم تذنبوا، لذهب الله بكم، وجاء بقوم يُذْنِبُونَ، فيستغفرون اللهَ تعالى، فيغفر لهم».رواه مسلم
عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "الْبَاقِيَاتُ الصَّالِحَاتُ، لَا إلَهَ إلَّا اللَّهُ، وَسُبْحَانَ اللَّهِ، وَاَللَّهُ أَكْبَرُ، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاَللَّهِ".رواه ابن حبان والحاكم، أما النسائي فرواه في الكبرى لكن من حديث أبي هريرة
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦ "አዛን ባዩን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለሌላ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዑሥማን ቢን አቢል ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በመምጣት "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰይጣን በኔና በሶላቴ እንዲሁም በቂረአቴ መካከል አዘናጋኝ። በኔ ላይም ያለባብስብኛል።" አላቸው። የአላህ መልዕክተኛም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ይሄ ሰይጣን ነው። ኺንዘብ ይባላል። ይህ ስሜት የተሰማህ ጊዜ ከርሱ በአላህ ተጠበቅ! ወደ ግራህም ሶስት ጊዜ ትፋ!" አሉት። እርሱም "ይህንን ፈፀምኩ አላህም አስወገደልኝ።" አለ።ሙስሊም ዘግበውታል።