Hadith for the World
ደረጃ ያላቸው ስራዎች

የእውቀት ትሩፋት

8 hadiths

8 hadiths

عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال: كان أخوانِ على عهد النبي صلى الله عليه وسلم وكان أحدُهما يأتي النبي صلى الله عليه وسلم والآخر يَحتَرِف، فَشَكَا الُمحتَرِف أَخَاه للنبي صلى الله عليه وسلم فقال: «لعَلَّك تُرزَقُ بِهِ».رواه الترمذي
عن أنس رضي الله عنه مرفوعاً: «من خَرج في طلب العلم فهو في سَبِيلِ الله حتى يرجع».رواه الترمذي
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል። የተጨነቀ ሰውን ከጭንቁ ለገላገለ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ጭንቀቱን ያቀልለታል። የሙስሊምን ነውር ለሸሸገ ሰው አላህም በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ነውሩን ይሸሽግለታል። የአላህ ባሪያ ወንድሙን በማገዝ ላይ እስከሆነ ድረስ አላህም ባሪያውን በማገዝ ላይ ነው። እውቀትን ለመፈለግ መንገድ የተጓዘ ሰው አላህም በርሱ ምክንያት የጀነትን መንገድ ያገራለታል። ሰዎች የአላህን መጽሐፍ ሊያነቡና በመካከላቸው ሊማማሩት ከአላህ ቤቶች መካከል አንድ ቤት ውስጥ እስከተሰባሰቡ ድረስ አላህም በነርሱ ላይ ሰኪናውን (እርጋታውን) ያወርድላቸዋል፤ በእዝነቱ ይሸፍናቸዋል፤ መላእክቶችም ያካብቧቸውና አላህም እርሱ ዘንድ ካሉት ጋር ያወሳቸዋል። ስራው ወደኋላ ያስቀረውን ሰው ዘሩ አያስቀድመውም።"»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሙዓዊያህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦ "አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል። እኔ አከፋፋይ ብቻ ነኝ አላህ ነው የሚሰጠው። ይህች ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ የቆመች ከመሆን አትወገድም! የአላህ ትእዛዝ እስክትመጣ ድረስም የተቃረናቸው ሁሉ አይጎዳቸውም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «النَّاسُ مَعَادِن كَمَعَادِن الذَّهَب وَالفِضَّة، خِيَارُهُم فِي الجَاهِلِيَّة خِيَارُهُم فِي الإِسْلاَم إِذَا فَقُهُوا، والأَرْوَاحُ جُنُودٌ مُجَنَّدَة، فَمَا تَعَارَفَ مِنْهَا ائتَلَفَ، وَمَا تَنَاكَرَ مِنْهَا اخْتَلَفَ». وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله -صلى الله عليه وسلم: «تَجِدُون النَّاسَ مَعَادِن: خِيَارُهُم فِي الجَاهِليَّة خِيَارُهُم فِي الإِسْلاَم إِذَا فَقِهُوا، وَتَجِدُون خِيَار النَّاس فِي هَذَا الشَّأْن أَشَدُّهُم كَرَاهِيَة لَه، وَتَجِدُون شَرَّ النَّاس ذَا الوَجْهَين، الَّذِي يَأْتِي هَؤُلاَء بِوَجه، وَهَؤُلاَء بِوَجْه».الحديث الأول: متفق عليه، ولفظه لمسلم؛ وروى البخاري أوله، وروى آخره عن عائشة -رضي الله عنها-. الحديث الثاني: متفق عليه
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!"ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
ከኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።"ሙስሊም ዘግበውታል።