Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ:

Available in 48 languages
«ከዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የርሳቸውን ሐዲሥ ሰምቶ ለሌላው እስኪያደርስ ድረስ የሸመደደ ሰው አላህ በዱንያ ውስጥ ውበትን፣ ቁንጅናና ብርሃንን እንዲሰጠው፤ በመጪው አለም ደግሞ ወደ ጀነት ብርሃን፣ ፀጋና ውበት አላህ እንዲያደርሰው ዱዓ አድጉለት። አንዳንዴ ሐዲሥ የሚነገረው ሰው ሐዲሡን መጀመርያ ከሰማው ሰው የበለጠ ሸምዳጅ፣ ተገንዛቢ፣ ከሐዲሡ ፍሬሃሳቦችን መዞ የሚያወጣ ይሆናል። በዚህም የመጀመሪያው ሰውዬ በአስተማማኝ መልኩ መሸምደዱንና "ነቅል" (መውሰድን) ሲችል ሁለተኛው ደግሞ በአስተማማኝ መልኩ መገንዘቡንና መረዳቱን የቻለ ይሆናል።

Source
ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality