Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦

Available in 55 languages
«ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ((የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለጀነት ነዋሪዎች በውስጧ እያሉ እንዲህ እንደሚል ነገሩን: "የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!" እነርሱም "ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል" በማለት ለርሱ ይመልሳሉ። እርሱም ለነርሱ: ተደሰታችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: አዎን ተደስተናል። ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው? ይላሉ። አላህም: ከዚህ የተሻለ ነገር ልስጣችሁን? ይላቸዋል። እነርሱም: ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ነገር ምን አለና? ይላሉ። እርሱም: ዘውታሪ የሆነውን ውዴታዬን አሰፍንባችኋለሁ። ከዚህ በኋላ በናንተ ላይ መቼም አልቆጣም። ይላቸዋል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality