Hadith for the World
ቀልብን አርጣቢ ምክሮችና ተግሳጾች

የጀነትና እሳት ባህሪዎች

17 hadiths

17 hadiths

ከዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «إنَّ في الجنَّة مائةَ دَرَجَة أعَدَّهَا الله للمُجاهِدين في سَبِيل الله ما بَيْنَ الدَّرَجَتَيْنِ كما بين السماء والأرض».رواه البخاري
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።" አቡ ሰዒድም በዚህች ንግግር ተደሰተና እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በድጋሚ ይንገሩኝ!" እርሳቸውም ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉ: "ሌላም አንድ ስራ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ ይደረጋል። በየሁሉም ደረጃ መካከልም ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።»ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس بن مالك رضي الله عنه مرفوعاً: «يُؤتى بأنعم أهل الدنيا من أهل النار يوم القيامة، فَيُصْبَغُ في النار صَبْغَةً، ثم يقال: يا ابن آدم، هل رأيت خيرًا قطُّ؟ هل مَرَّ بك نَعِيمٌ قطُّ؟ فيقول: لا والله يا رب، وَيُؤْتَى بأشدِّ الناس بُؤسًا في الدنيا من أهل الجَنَّة، فَيُصْبَغُ صَبْغَةً في الجنَّة، فيقال له: يا ابن آدم، هل رأيت بُؤسًا قط؟ هل مَرَّ بك شِدَّةٌ قط؟ فيقول: لا والله، ما مَرَّ بي بُؤْسٌ قطٌّ، ولا رأيت شِدةً قَطُّ».رواه مسلم
عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه مرفوعاً: «يُؤْتَى بجهنم يومئذ لها سبعون ألف زِمَامٍ مع كل زمام سبعون ألف ملك يَجُرُّونَهَا».رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : « سَيْحَانُ وَجَيْحَانُ وَالفُرَاتُ والنِّيل كلٌّ من أنهار الجنة».رواه مسلم
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይና ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «(ለጀነት ነዋሪዎች) አንድ ተጣሪ ይጣራና "ለናንተ ጤና አላችሁ መቼም አትታመሙም፤ ለናንተ ህይወት አላችሁ መቼም አትሞቱም፤ ለናንተ ወጣትነት አላችሁ መቼም አታረጁም፤ ለናንተ በፀጋ ውስጥ መጣቀም አላችሁ መቼም አትቸገሩም።" ይህም ይህ የአላህ ዐዘ ወጀል ንግግር ነው: {ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ።} [አልአዕራፍ: 43]»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ተባረከ ወተዓላ ለጀነት ነዋሪዎች እንዲህ ይላቸዋል: 'እናንተ የጀነት ነዋሪዎች ሆይ!' እነርሱም 'ደጋግመን በደስተኝነት አቤት ብለናል' ይላሉ። አላህም 'ተደሰታችሁን?' ይላቸዋል። እነርሱም 'ከፍጥረታቶችህ ለአንድም አካል ያልሰጠኸውን ሰጥተኸን እንዴት ነው የማንደሰተው?' ይላሉ። እርሱም 'እኔ ከዚህም የተሻለ ነገር እሰጣችኋለሁ።' ይላል። እነርሱም 'ጌታችን ሆይ! ከዚህ የተሻለ ምን አይነት ነገር ይኖራል?' ይላሉ። አላህም 'በናንተ ላይ ውዴታዬን አሰፍናለሁ። በናንተ ላይ ከዚህ በኋላ መቼም አልቆጣም።' ይላቸዋል።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በዒድ አልአድሓ ወይም በዒድ አልፈጥር ወደ መስገጃ ስፍራ ሲሄዱ በሴቶች በኩል አለፉና እንዲህም አሉ: "እናንተ የሴቶች ስብስቦች ሆይ! ምጽዋት ስጡ! እኔ አብዛኛው የእሳት ነዋሪዎች ሆናችሁ አይቻችኋለሁ።" ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በምን ምክንያት?" አሉ። እርሳቸውም "እርግማን ታበዛላችሁ፤ አኗኗሪን ትክዳላችሁ። አይምሮና ዲናቸው የጎደለ ሆኖ፤ ቆራጥ የሆነን ወንድ ልጅ ልብ የሚወስድም እንደናንተ አልተመለከትኩም!" አሉ። ሴቶቹም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዲናችንና አይምሯችን መጉደል ምንድን ነው?" አሉ። እርሳቸውም "የአንድ ሴት ልጅ ምስክር እንደ ግማሽ የወንድ ምስክር አይደለም የሚቆጠረው?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የአይምሮዋ መጉደሉ ነው። የወር አበባ ባየች ጊዜ አትሰግድምም አትጾምም አይደል?" አሉ። ሴቶቹም "እንዴታ!" አሉ። እርሳቸውም "ይህም የዲናቸው መጉደሉ ነው።" አሉ።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ ተባረከ ወተዓላ እንዲህ ብሏል: "ደጋግ ለሆኑ ባሪያዎቼ ዓይን ያላየችው፤ ጆሮ ያልሰማችው፤ በሰው ቀልብ ላይ ውል ያላለን ፀጋ አዘጋጅቼላቸዋለሁ።"» «አቡ ሁረይራም እንዲህ አለ: "ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {ይሰሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለነርሱ የተደበቀላቸውን (ፀጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም።} [አስሰጅዳ:17]"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عياض بن حمار المجاشعي رضي الله عنه ، أن رسول الله صلى الله عليه وسلم ، قال ذات يوم في خطبته: «ألَا إن ربي أمرني أن أُعَلِّمَكم ما جَهِلتم، ممَّا علَّمني يومي هذا، كلُّ مالٍ نَحَلتُه عبدًا حلال، وإني خلقتُ عبادي حُنَفاء كلهم، وإنهم أتتهم الشياطين فاجتالتهم عن دينهم، وحَرَّمت عليهم ما أحللتُ لهم، وأمرتهم أن يُشركوا بي ما لم أُنزِّل به سلطانا، وإن الله نظر إلى أهل الأرض، فمَقَتهم عربهم وعَجَمهم، إلَّا بقايا من أهل الكتاب، وقال: إنما بعثتُك لأبتليَك وأبتلي بك، وأنزلتُ عليك كتابًا لا يغسله الماءُ، تقرؤه نائمًا ويقظان، وإنَّ اللهَ أمرني أن أحرِق قُرَيشًا، فقلت: رب إذا يَثْلُغوا رأسي فيدعوه خُبْزة، قال: استخرجهم كما استخرجوك، واغزهم نُغزك، وأنفق فسننفق عليك، وابعث جيشا نبعث خمسة مثله، وقاتل بمن أطاعك مَن عصاك، قال: وأهل الجنة ثلاثة ذو سلطان مُقْسِط مُتَصَدِّق مُوَفَّق، ورجل رحيم رقيق القلب لكل ذي قربى ومسلم، وعفيف متعفِّف ذو عيال، قال: وأهل النار خمسة: الضعيف الذي لا زَبْر له، الذين هم فيكم تبعا لا يبتغون أهلا ولا مالا، والخائن الذي لا يخفى له طمع، وإن دقَّ إلا خانه، ورجل لا يُصبح ولا يمسي إلا وهو يخادعك عن أهلك ومالك «وذكر» البخل أو الكذب والشِّنظير الفحَّاش».رواه مسلم
عن عبد الله بن عمر رضي الله عنهما أنَّ رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «عُذِّبت امرأة في هِرَّة سَجَنَتْها حتى ماتت، فدخلت فيها النار، لا هي أطعمتها ولا سَقتها، إذ حبستها، ولا هي تَركتْها تأكل مِن خَشَاشِ الأرض».متفق عليه
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "የምድራችሁ እሳት ከጀሀነም እሳት ሰባ ክፍል አንዷ ክፍል ናት።" "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የምድር እሳት ለቅጣት) በቂ ነበረች’እኮ" ተባሉ። እሳቸውም፦ "የጀሀነም እሳት ከምድር እሳት በስልሳ ዘጠኝ ክፍል እንድትበልጥ ተደርጋለች። ሁሉም ክፍል የምድር እሳት አምሳያ ሀሩርነት (አቃጣይነት) ነው ያላቸው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَبِرَسُولِهِ، وَأَقَامَ الصَّلاَةَ، وَصَامَ رَمَضَانَ كَانَ حَقًّا عَلَى اللَّهِ أَنْ يُدْخِلَهُ الجَنَّةَ، جَاهَدَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَوْ جَلَسَ فِي أَرْضِهِ الَّتِي وُلِدَ فِيهَا»، فَقَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَفَلاَ نُبَشِّرُ النَّاسَ؟ قَالَ: «إِنَّ فِي الجَنَّةِ مِائَةَ دَرَجَةٍ، أَعَدَّهَا اللَّهُ لِلْمُجَاهِدِينَ فِي سَبِيلِ اللَّهِ، مَا بَيْنَ الدَّرَجَتَيْنِ كَمَا بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ، فَإِذَا سَأَلْتُمُ اللَّهَ فَاسْأَلُوهُ الفِرْدَوْسَ، فَإِنَّهُ أَوْسَطُ الجَنَّةِ وَأَعْلَى الجَنَّةِ -أُرَاهُ- فَوْقَهُ عَرْشُ الرَّحْمَنِ، وَمِنْهُ تَفَجَّرُ أَنْهَارُ الجَنَّةِ».رواه البخاري