Hadith for the World
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ቀልብን አርጣቢ ምክሮችና ተግሳጾች

63 hadiths

63 hadiths

ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس بن مالك رضي الله عنه أنَّ رَجُلاً كَانَ عِند النَبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَمَرَّ رَجُلٌ بِهِ، فقال: يا رسول الله، أنِّي لَأُحِبُّ هَذَا، فَقَال لَهُ النَبِيُّ صلى الله عليه وسلم : «أَأَعْلَمْتَهُ؟» قال: لا. قال: «أَعْلِمْهُ»، فَلَحِقَهُ، فقال: إِنِّي أُحِبُّك فِي الله، فقال: أّحَبَّك الَّذِي أَحْبَبْتَنِي لَهُ.رواه أبو داود والنسائي في الكبرى وأحمد
عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قَالَ: قالَ رسول اللَّه -صَلّى اللهُ عَلَيْهِ وسَلَّم-: «إِنَّ مِنْ إِجْلاَلِ الله -تَعَالَى-: إِكْرَامَ ذِي الشَّيْبَةِ المُسْلِمِ، وَحَامِلِ القُرْآنِ غَيرِ الغَالِي فِيه، وَالجَافِي عَنْه، وَإِكْرَام ذِي السُّلْطَان المُقْسِط».رواه أبو داود
ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ! የበኒ ኢስራኢሎች የመጀመሪያ ፈተና የተከሰተው በሴቶች ነበርና።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما مرفوعاً: «ليس منا من لم يَرحمْ صغيرنا، ويَعرفْ شَرَفَ كبيرنا».رواه أبو داود والترمذي وأحمد
ከአነስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ ትንሳኤ እለት ጠየቃቸው። "ትንሳኤ መቼ ነው?" አላቸው። እርሳቸውም "ለርሷ ምን አዘጋጅተሀል?" አሉት። እርሱም "እኔ አላህና መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመውደዴ ውጭ ምንም ነገር አላዘጋጀሁም።" አለ። እርሳቸውም "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" አሉት። አነስም እንዲህ አሉ፦ "በዚህ "አንተ ከወደድካቸው ጋር ነህ።" በሚለው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ንግግር እንደተደሰትነው በምንም አልተደሰትንም።" ቀጥሎም (አነስ) እንዲህ አሉ: "እኔ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና)፣ አቡበከርንና ዑመርን እወዳለሁ። እነርሱ የሰሩትን አምሳያ ባልሰራ እንኳ እነርሱን በመውደዴ ከነርሱ ጋር መሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። ሽቶ ተሸካሚ ወይ ይሰጥሀል፣ ወይ ትገዛዋለህ፣ ወይ ከርሱ መልካም መአዛን ታገኛለህ። ወናፍ ነፊ ደግሞ ወይ ልብስህን ያቃጥላል ወይም ከርሱ መጥፎ ሽታን ታገኛለህ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም። ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ ያመሰግንና ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ጉዳት በሚያጋጥመውም ጊዜ ይታገስና ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ፤ ብቸኛና አጋርም እንደሌለው፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛው መሆናቸውን፤ ዒሳም የአላህ ባሪያና መልክተኛው፣ ወደመርየምም ያስተላለፈው ቃሉና ከርሱ የሆነ መንፈስ መሆኑን፣ ጀነትም እውነት መሆኗን፣ እሳትም እውነት መሆኗን የመሰከረ ሰው በማንኛውም ስራ ላይ ሆኖም አላህ ጀነት ያስገባዋል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن معاذ بن جبل رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم أنه قال: «قَالَ اللهُ -عَزَّ وجَلَّ-: المُتَحَابُّون فِي جَلاَلِي، لَهُم مَنَابِرُ مِن نُورٍ يَغْبِطُهُم النَبِيُّونَ والشُهَدَاء».رواه الترمذي وأحمد
ከኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ለአማኞች እስር ቤት ለከሃዲዎች ጀነት ናት።"»ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «إنَّ في الجنَّة مائةَ دَرَجَة أعَدَّهَا الله للمُجاهِدين في سَبِيل الله ما بَيْنَ الدَّرَجَتَيْنِ كما بين السماء والأرض».رواه البخاري
عن سهل بن سعد الساعدي ـرضي الله عنه- قَالَ رَسُول اللَّه -صَلّى اللهُ عَلَيْهِ وسَلَّم-: «لو كانت الدنيا تَعدل عند الله جَناح بَعوضة، ما سَقَى كافراً منها شَرْبَة ماء».رواه الترمذي
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ 'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል። ይፋ ከማውጣትም መካከል ሰውዬው ምሽት ላይ አንድ ወንጀልን ይሰራል ከዚያም አላህ ለርሱ (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ‹እከሌ ሆይ! ትናንት ምሽት እንዲህ እንዲህ ሰራሁ።› ይላል። ጌታው (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ ከራሱ ላይ የሚገፍ ሆኖ ያነጋል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከመሞታቸው ሶስት ቀናት በፊት እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: «"አንተ አቡ ሰዒድ ሆይ! በአላህ ጌትነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት፣ በሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው ለርሱ ጀነት ግድ ሆናለታለች።" አቡ ሰዒድም በዚህች ንግግር ተደሰተና እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በድጋሚ ይንገሩኝ!" እርሳቸውም ደገሙለትና አክለውም እንዲህ አሉ: "ሌላም አንድ ስራ አለች። አንድ ባሪያ በርሷ ሰበብ ጀነት ውስጥ መቶ ደረጃ ከፍ ይደረጋል። በየሁሉም ደረጃ መካከልም ያለው ርቀትም በሰማይና በምድር መካከል እንዳለው ርቀት ነው።" እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናት እርሷ?" አለ። እርሳቸውም "በአላህ መንገድ መታገል! በአላህ መንገድ መታገል!" አሉት።»ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس رضي الله عنه مرفوعاً: «يَتْبَعُ الميتَ ثلاثةٌ: أهْلُه ومَالُه وعَمَلُه، فيرجع اثنان ويَبْقى واحد: يرجع أهْلُه ومَالُه، ويبقى عَمَلُه».متفق عليه
عن أنس بن مالك رضي الله عنه مرفوعاً: «يُؤتى بأنعم أهل الدنيا من أهل النار يوم القيامة، فَيُصْبَغُ في النار صَبْغَةً، ثم يقال: يا ابن آدم، هل رأيت خيرًا قطُّ؟ هل مَرَّ بك نَعِيمٌ قطُّ؟ فيقول: لا والله يا رب، وَيُؤْتَى بأشدِّ الناس بُؤسًا في الدنيا من أهل الجَنَّة، فَيُصْبَغُ صَبْغَةً في الجنَّة، فيقال له: يا ابن آدم، هل رأيت بُؤسًا قط؟ هل مَرَّ بك شِدَّةٌ قط؟ فيقول: لا والله، ما مَرَّ بي بُؤْسٌ قطٌّ، ولا رأيت شِدةً قَطُّ».رواه مسلم
ከነዋስ ቢን ሰምዓን አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለበጎ ተግባርና ስለወንጀል ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም " በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።»ሙስሊም ዘግበውታል።