Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

Available in 65 languages
«ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዓንሁማ) አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ትላልቅ ወንጀሎች፦ በአላህ ማጋራት፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል፣ ነፍስ ማጥፋትና የውሸት መሀላ ናቸው።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለትላልቅ ወንጀሎች አብራሩ። ትልቅ ወንጀል የሚባለውም ሰሪው በዱንያ ወይም በአኺራ ስለሚቀጣው ቅጣት ከባድ ዛቻ የተዛተበት ነው። የመጀመሪያውም:- "በአላህ ማጋራት ነው።" ይህም ከአምልኮ አይነቶች መካከል ማንኛውንም አምልኮ ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል መስጠት ፤ እንዲሁም ከአላህ ውጪ የሆነን አካል በተመላኪነቱ ፣ በጌትነቱ ወይም በስምና ባህሪያቱ አላህ በተለየበት ነገር ላይ ከአላህ ጋር እኩል ማድረግ ማለት ነው። ሁለተኛው:- "የወላጆችን ሐቅ ማጓደል": ይህም ማንኛውም ወላጆችን ወደ ማወክ የሚዳርግ ንግግርም ይሁን ተግባር መፈፀምና ለነርሱ በጎ ማድረግን መተው ማለት ነው። ሶስተኛው: "ነፍስን ያለ አግባብ ማጥፋት ነው።" ይህም በግፍ ወይም ወሰን በማለፍ መግደል ማለት ነው። አራተኛው: "(የሚን አልገሙስ) አስማጭ መሀላ ነው።" ይህም እየዋሸ እንደሆነ እያወቀ በውሸት መማል ነው። በዚህም ስያሜ የተጠራበት ምክንያት ሰውየውን ወንጀል ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ ስለምታሰምጠው ነው።

Source
ቡኻሪ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality