Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰማ:

Available in 61 languages
«ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰማ: "አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል። በሚገባ ወቅት አላህን ሳያወሳ የገባ እንደሁ ሰይጣን 'ማደሪያ አግኝታችኋል' ይላል። በሚበላበት ወቅትም አላህን ካላወሳ ደግሞ 'ማደሪያም እራትም አግኝታችኋል።' ይላል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቤት በሚገባ ወቅትና ምግብ ከመመገባችን በፊት አላህን ማውሳት አዘዙ። እርሱ ቤት በሚገባ ወቅትና ምግቡን በሚጀምር ወቅት አላህን (ቢስሚላህ) በማለት ያወሳ ጊዜ ሰይጣን ለግብረ አበሮቹ "እዚህ ባለቤቱ አላህን በማውሳት ከናንተ የተጠበቀበት በሆነው ቤት ውስጥ ምንም ማደሪያም እራትም የላችሁም።" ይላቸዋል። ሰውዬው ቤቱ በሚገባ ወቅትና ምግብ በሚመገብበት ወቅት አላህን ካላወሳ ግን ሰይጣን ለግብረአበሮቹ እዚህ ቤት ውስጥ ማደሪያም እራትም እንዳገኙ ይነግራቸዋል።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality