Hadith for the World
የዱዓና አዝካር ፊቅህ

አላህን የማውሳት ጥቅሞች

8 hadiths

8 hadiths

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰማ: "አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል። በሚገባ ወቅት አላህን ሳያወሳ የገባ እንደሁ ሰይጣን 'ማደሪያ አግኝታችኋል' ይላል። በሚበላበት ወቅትም አላህን ካላወሳ ደግሞ 'ማደሪያም እራትም አግኝታችኋል።' ይላል።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል "አላህ እንዲህ አለ: እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። ለብቻው ካወሳኝ ለብቻዬ አወሳዋለሁ፤ በህብረት ካወሳኝ ደሞ ከርሱ የተሻለ በሆኑ ህብረቶች ዘንድ አወሳዋለሁ። አንድ ስንዝር ወደኔ ከቀረበ አንድ ክንድ ወደርሱ እቀርባለሁ። አንድ ክንድ ወደኔ ከቀረበ እጅ ሙሉ ወደርሱ እቀርባለሁ። እየተራመደ ወደኔ ከመጣ በሶምሶማ ወደርሱ እመጣለሁ።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ነበርን። እንዲህም አሉን: "አንዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ መሸመት ይሳነዋልን?" ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንድ ጠያቂ "እንዴት ነው አንዳችን አንድ ሺህ ምንዳ የሚሸመተው?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም: "መቶ ጊዜ ተስቢሕ ካለ ለርሱ አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል ወይም ከርሱ ላይ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰረዝለታል።" በማለት መለሱ።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው ምሳሌ እንደ ህያውና እንደ ሞተ ሰው ምሳሌ ነው።"» በሙስሊም ዘገባ ደሞ "በውስጡ አላህ የሚወሳበት ቤትና አላህ የማይወሳበት ቤት ምሳሌ እንደ ህያውና እንደሞተ ሰው ምሳሌ ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن زيد مولى رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «من قال: أَسْتَغْفِرُ الله الذي لا إله إلا هو الحَيَّ القيَّومَ وأتوب إليه، غُفرت ذنوبه، وإن كان قد فَرَّ من الزَّحْف».رواه أبو داود والترمذي
አቢ ማሊክ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። ፍትሃዊ መሪ፤ አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት፤ ቀልቡ ወደ መስጂዶች የተንጠለጠለ ሰውዬ፤ በአላህ መንገድ የተገናኙ በርሱም መንገድ የተለያዩ ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፤ የተከበረችና ቆንጆ የሆነች ሴት ለዝሙት ጠርታው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለ ሰውዬ፤ ቀኙ የምትሰጠውን ግራው እስከማታውቅ ድረስ ምፅዋቱን በመደበቅ ምፅዋት የመፀወተ ሰውዬ፤ አላህን ገለል ብሎ አውስቶ አይኖቹ ያነቡ ሰውዬ ናቸው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።