Hadith for the World
የዱዓና አዝካር ፊቅህ

ከመስጂድ ሲገባና ሲወጣ የሚባሉ ዚክሮች

2 hadiths

2 hadiths

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን አልዐስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተላለፈው: እርሳቸው መስጂድ በሚገቡ ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር: "አዑዙ በላሂል ዐዚም ወቢወጅሂሂል ከሪም ወሱልጧኒሂል ቀዲም ሚነሽ-ሸይጧኒ ረጂም" "የሚሉት ይህን ብቻ ነውን? " ተብሎ ተጠየቀ። "አዎን" አልኩኝ። "ይህን ያለ ጊዜም ሸይጧን 'የቀረውን የቀኑን ክፍል ከኔ ተጠበቀ።' ይላል።" ትርጉሙም "ታላቅ በሆነው አላህ፣ በተከበረው ፊቱ፣ መጀመሪያም በሌለው ስልጣኑ ከተረገመው ሰይጣን እጠበቃለሁ።"አቡዳውድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሑመይድ ወይም አቡ ኡሰይድ እንደተዘገበው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"ሙስሊም ዘግበውታል።