Hadith for the World
የዱዓና አዝካር ፊቅህ

የንጋትና ምሽት ዚክሮች

4 hadiths

4 hadiths

عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه قال: كان نبي الله صلى الله عليه وسلم إذا أمسى قال: «أمسينا وأمسى الملك لله، والحمد لله، لا إله إلا الله وحده لا شريك له» قال الراوي: أَرَاهُ قال فِيهِنَّ: «له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير، ربِّ أسألك خير ما في هذه الليلة وخير ما بعدها، وأعوذ بك من شر ما في هذه الليلة وشر ما بعدها، رب أعوذ بك من الكسل، وسُوءِ الكِبَرِ، رب أعوذ بك من عذاب في النار، وعذاب في القبر»، وإذا أصبح قال ذلك أيضا «أصبحنا وأصبح الملك لله».رواه مسلم
ከሸዳድ ቢን አውስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ 'አልላሁመ አንተ ረቢ ላ ኢላሃ ኢላ አንተ፣ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዓላ ዐህዲከ ወወዕዲከ ማስተጦዕቱ፣ አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማ ሶነዕቱ፣ አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፣ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ፣ ፈኢነሁ ላየግፊሩዝ-ዙኑበ ኢላ አንተ።' ማለትህ ነው።'" እንዲህም ብለዋል "በርሷ አምኖ ቀን ላይ ያላትና በዛው ቀን ከማምሸቱ በፊት የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው። በርሷ አምኖ ምሽት ላይ ያላትና ከማንጋቱ በፊት የሞተ ሰውም እርሱ ከጀነት ባለቤቶች ነው።" (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ፈጥረሀኛል እኔም ባሪያህ ነኝ፣ እኔ በቻልኩት መጠን በቃል ኪዳንህ ላይ እገኛለሁ፤ ከሰራሁት ክፋት በአንተ እጠበቃለሁ፣ በኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ አረጋግጣለሁ፣ ወንጀሌንም ላንተ አረጋግጣለሁና ማረኝ! እነሆ ካንተ በቀር ወንጀሎችን የሚምር የለምና።)ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ኹበይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "በዝናባማና በድቅድቅ ጨለማ ምሽት የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እኛን እንዲያሰግዱን ፈልገን ወጣን። አገኘኋቸውና 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። ቀጥለውም 'በል!' አሉኝ። ምንም አላልኩኝም። አሁንም 'በል!' አሉኝ። እኔም ምን ልበል? አልኳቸው። እርሳቸውም 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።"አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።
ከአቢ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "በምሽት ውስጥ የመጨረሻዎቹን የበቀራህ ምእራፍ ሁለት አንቀፆች የቀራ ሰው ይበቁታል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።