Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡

Available in 60 languages
«ከከዕብ ቢን ዑጅራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገራቸው የማይከስርበትንና የማይፀፀትበትን ዚክር ተናገሩ። እንደውም በቃላቶቹ ምንዳ የሚያገኝባቸው ናቸው። ከፊሉ ከከፊሉ በኋላ የሚባሉ ሲሆኑ ከግዴታ ሶላት በኋላ ነው የሚባሉት። እነርሱም: "ሱብሐነላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት። ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው። "አልሐምዱሊላህ"ን ሰላሳ ሶስት ጊዜ ማለት ነው። ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በተሟላ ምሉዕነት መግለፅ ነው። "አላሁ አክበር"ን ሰላሳ አራት ጊዜ ማለት ነው። አላህ ከሁሉም ነገር ታላቅና የላቀ ነውና።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality