AM
ቀልብን አርጣቢ ምክሮችና ተግሳጾች
ነፍስን ማጥራት
9 hadiths
የቀልብ ተግባራት
14
الزهد والورع
2
የደጋጎች ሁኔታ
4
ወንጀለኞችን ማውገዝ
6
ዱንያን ከመውደድ ማውገዝ
8
ከዝንባሌና ስሜት ማውገዝ
1
ተውበት
3
ነፍስን ማጥራት
9
የጀነትና እሳት ባህሪዎች
17
9 hadiths
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»
ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም። ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ ያመሰግንና ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ጉዳት በሚያጋጥመውም ጊዜ ይታገስና ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉ: "በዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ ወይም እንደ መንገድ አላፊ ሁን።" ኢብኑ ዑመርም እንዲህ ይል ነበር "ስታመሽ ንጋትን አትጠብቅ፣ ስታነጋ ምሽትን አትጠብቅ፣ በጤንነትህ ለበሽታህ ስንቅ ያዝ፣ በህይወትህ ለሞትህ ስንቅ ያዝ።"»
ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ። ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለው፤ እርዳታ አይንፈገው፤ አያሳንሰው።" ወደ ደረታቸው እየጠቆሙም ሶስት ጊዜ "አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው።" አሉ። "ሰውዬው ሙስሊም ወንድሙን አሳንሶ መመልከቱ መጥፎ ሠራ ለመባል ይበቃዋል። ሁሉም ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ደሙ፣ ገንዘቡና ክብሩ እርም ነው።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"
ቡኻሪ ዘግበውታል።
አቢ ማሊክ አልአሽዐሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ንፅህና የኢማን ግማሽ ነው 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው) የሚለው ሚዛን ይሞላል፤ 'ሱብሐነላህ ወል'ሐምዱ ሊላህ' (አላህ ጥራት የተገባው ነው፤ ምስጋናም ሁሉ ለአላህ ነው) የሚለው በሰማያትና በምድር መካከል ያለውን ይሞላሉ ወይም ይሞላል ፤ ሰላት ብርሃን ነው፣ ምጽዋት ማስረጃ ነው፣ ትዕግስት ወገግታ (አንፀባራቂ ብርሃን) ነው፣ ቁርኣን ላንተ ወይም በአንተ ላይ ማስረጃ ነው። ሁሉም ሰው በማለዳ ወጥቶ ነፍሱን ይሸጣል። ወይ ከጥፋት ነፃ ያወጣታል ወይም ወደ ጥፋት ይጥላታል። "
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሱፍያን ቢን ዐብደላህ አሥሠቀፊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ከርሶ ውጪ ስለርሱ አንድንም ሰው የማልጠይቀው የሆነን አንድን ንግግር ንገሩኝ አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ አምኛለሁ በል ከዚያም ቀጥ በል።' አሉኝ"
ሙስሊምና አሕመድ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። ፍትሃዊ መሪ፤ አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት፤ ቀልቡ ወደ መስጂዶች የተንጠለጠለ ሰውዬ፤ በአላህ መንገድ የተገናኙ በርሱም መንገድ የተለያዩ ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፤ የተከበረችና ቆንጆ የሆነች ሴት ለዝሙት ጠርታው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለ ሰውዬ፤ ቀኙ የምትሰጠውን ግራው እስከማታውቅ ድረስ ምፅዋቱን በመደበቅ ምፅዋት የመፀወተ ሰውዬ፤ አላህን ገለል ብሎ አውስቶ አይኖቹ ያነቡ ሰውዬ ናቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።