Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:

Available in 49 languages
«ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ በሰዎች ላይ ከዋላቸው ፀጋዎች መካከል አብዛኛው ሰው ያለ አግባብ በመጠቀም ስለሚከስርባቸው ሁለት ትላልቅ ፀጋዎች ተናገሩ። የሰው ልጅ የጤንነት ፀጋ ነፃ (ከትርፍ) ጊዜ ጋር አብሮ ሲሰበሰቡለት አብዛኛውን ጊዜ ከአምልኮ ሲሳነፍ ነው የሚገኘው። ይህ ክስረት ነው። የአብዛኛው ሰው ሁኔታም እንዲሁ ነው። ትርፍ ወቅቱንና ጤንነቱን አላህን በማምለክ ከተጠቀመበት ግን ዱንያ የመጪው አለም መዝሪያ ናትና ትርፋማ ይሆናል። ዱንያ ውስጥ ትርፉ በመጪው አለም የሚገኝበት ንግድ አለ። ትርፍ ወቅት ከጊዜ በኋላ መጠመድ ይከተለዋል። ጤንነትም በሽታ ይከተለዋል። ሌላው ቀርቶ እርጅና ብቻ እንኳ መምጣቱ በቂ ነው።

Source
ቡኻሪ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality