Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡

Available in 55 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአሏህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡ "አማኝ የሆነ ወንድና ሴት በርሱ ላይ ምንም ወንጀል የሌለበት ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስ በነፍሱ፣ በልጁና በገንዘቡ ላይ መከራ ከመከሰት አይወገድም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አማኝ የሆነ ወንድና ሴት ባሪያ ከፈፀማቸው ሁሉም ወንጀሎችና ኃጢዐቶች የፀዳ ሆኖ አላህን እስኪገናኝ ድረስና በነዚህ መከራዎች ሁሉንም ወንጀሎቹን አላህ እስኪምረው ድረስ በነፍሱ (በጤናውና በአካሉ)፣ በልጆቹ (በህመም ወይም ሞት ወይም በነርሱ በመበደል ወይም ከዚህ ውጪ ባሉ በልጆች ሳቢያ በሚደርሱ መከራዎች)፣ በገንዘቡ (በመደኽየት፣ ንግዱን በመክሰር፣ በመሰረቅ፣ በኑሮ መወደድ፣ በሲሳይ መጥበብ) የሚያጋጥመው መከራና ፈተና አይላቀቀውም ብለው ተናገሩ።

Source
ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality