Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 60 languages
«ከሱሀይብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም። ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ ያመሰግንና ለርሱ መልካም ይሆንለታል። ጉዳት በሚያጋጥመውም ጊዜ ይታገስና ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድናቆታዊ በሆነ መልኩ በአማኝ ጉዳይና ሁኔታ ይገረማሉ። ይህም የአማኝ ሁኔታዎች ባጠቃላይ መልካም በመሆናቸው ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ አይሆንም። አማኝ የሆነ ሰው ደስታ በሚያጋጥመው ጊዜ በርሱ ላይ አላህን ያመሰግናል። በማመስገኑም ምንዳን ያገኛል። ጉዳት ሲያጋጥመው ደግሞ ይታገሳልም አላህ ዘንድ ምንዳ አገኝበታለሁ ብሎም ያስባል። በትእግሰቱም ምንዳን ያገኛል። ስለዚህ እርሱ በሁሉም ሁኔታዎቹ በምንዳ ላይ ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality