Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡

Available in 71 languages
«ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኡመታቸውን ከሰባት አጥፊ ወንጀሎች እንዲርቁ አዘዙ። ምን ምን እንደሆኑ በተጠየቁ ጊዜም ተከታዮቹን ዘረዘሩ፡ የመጀመሪያው : በየትኛውም መልኩ ቢሆን ጥራት ለተገባው አላህ ቢጤን በማድረግ፤ ከአምልኮዎች መካከል ማንኛውም የአምልኮ ዘርፍን ከአሏህ ውጭ ላለ አካል በመስጠት አላህ ላይ ማጋራት መሆኑን ገለፁ፤ በሽርክ የጀመሩበት ምክንያትም ከወንጀሎች ሁሉ ትልቁ ወንጀል ስለሆነ ነው። ሁለተኛ ድግምት፡ - እየቋጠሩ፣ እያነበነቡ፣ መድኃኒትና ጭሳጭስ እያደረጉ የሚሸርቡትን የሚጠቁም ገላጭ ቃል ሲሆን - ድግምቱ የተደረገበትን ሞት ወይም ህመም ላይ በመጣል፣ ወይም በባልና ሚስት መካከል መለያየትን በመፍጠር ተፅእኖ የሚያሳድር ነው። ድርጊቱ ሰይጣናዊ ስራም እንደመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ በሽርክ እና መጥፎ መናፍስት የሚወዱትን ነገር እያደረጉ ወደነርሱ በመቃረብ የሚከናወን ነው። ሶስተኛ አስተዳደሩ ተግባራዊ በሚያደርገው ሸሪዓዊ ምክንያት ካልሆነ በቀር አሏህ እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል ነው። አራተኛ በመብላትም ይሁን በሌላ መልኩ በመጠቃቀም ወለድን መውሰድ ነው። አምስተኛ ለአቅመ አዳም ሳይደርስ አባቱ በሞተበት ታዳጊ ገንዘብ ላይ ወሰን ማለፍ ነው። ስድስተኛ ከከሀዲያን ጋር ከሚደረገ ፍልሚያ ማፈግፈግ ነው። ሰባተኛ ጥብቅ የሆኑ ጨዋ እንስቶችን መዝለፍ፤ እንደዚሁም ጨዋ ወንዶችን መዝለፍ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality