AM
ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ
ውግዝ ስነ-ምግባር
21 hadiths
ምስጉን ስነ-ምግባር
35
ውግዝ ስነ-ምግባር
21
21 hadiths
ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: «أتدرون من المفلس؟» قالوا: المُفْلِس فينا من لا دِرهَمَ له ولا مَتَاع، فقال: «إن المفلس من أمتي من يأتي يوم القيامة بصلاة وصيام وزكاة، ويأتي وقد شَتَمَ هذا، وقذف هذا، وأكل مال هذا، وسَفَكَ دم هذا، وضرب هذا، فيعطى هذا من حسناته، وهذا من حسناته، فإن فنيت حسناته قبل أن يُقْضَى ما عليه، أخذ من خطاياهم فَطُرِحتْ عليه، ثم طُرِحَ في النار».
رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሱለይማን ቢን ሱረድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ተቀምጬ ሳለ ሁለት ሰዎች ይሰዳደባሉ። አንዱ ፊቱ ቀልቷል፣ ደም ስሩ ተገታትሯል። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ "እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።" ለርሱም ሄደው "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ" እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም "እኔ ላይ እብደት አለብኝ እንዴ?" አላቸው።»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ابن عمر رضي الله عنهما مرفوعا: «الظلم ظلمات يوم القيامة». عن جابر رضي الله عنهما مرفوعا: «اتقوا الظلم، فإن الظلم ظلمات يوم القيامة، واتقوا الشُّحَ؛ فإنه أَهْلَكَ من كان قبلكم».
حديث ابن عمر -رضي الله عنهما-: متفق عليه. حديث جابر -رضي الله عنه-: رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) የአላህ ባሮች ሆይ! ወንድማማቾች ሁኑ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊምን መስደብ አመፀኝነት ነው። መግደሉ ክህደት ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «من الكبائر شَتْمُ الرجل والديه» قيل: وهل يسبّ الرجل والديه؟ قال: «نعم، يسبّ أبا الرجل فيسبّ أباه، ويسبّ أمّه، فيسبّ أمّه».
متفق عليه
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ከሰዎች ሁሉ አላህ ዘንድ እጅግ የተጠላው ደረቅ ተከራካሪ የሆነ ሰው ነው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'አላህ በዳይን ያዘገየዋል። የያዘው ጊዜ ግን አይለቀውም!'" አቡ ሙሳ እንዲህ አለ: "ቀጥለውም {የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው። ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው።} [ሁድ: 102] የሚለውን አነበቡ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعًا: «بينما رجل يمشي في حُلَّةٍ تُعْجِبُهُ نَفْسُهُ، مُرَجِّلٌ رأسه، يَخْتَالُ في مَشْيَتهِ، إذ خَسَفَ اللهُ به، فهو يَتَجَلْجَلُ في الأرض إلى يوم القيامة".
متفق عليه
عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه عن النبيِّ صلى الله عليه وسلم ، قَالَ: «لا يدخلُ الجنةَ مَن كان في قلبه مِثقال ذرةٍ من كِبر» فقال رجل: إنّ الرجلَ يحب أن يكون ثوبه حسنا، ونَعله حسنة؟ قال: «إنّ الله جميلٌ يحب الجمالَ، الكِبر: بَطَرُ الحق وغَمْطُ الناس».
رواه مسلم
ከሰሙራ ቢን ጁንዱብና ሙጚራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ውሸት መሆኑን እያወቀ ከኔ አንድ ሐዲሥን ያወራ ሰው ከውሸታሞች አንዱ ነው።"»
رواه مسلم في مقدمته
ከሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: ሂሻም በሻም ውስጥ በሚገኙ ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች ፀሐይ ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ሰዎች በኩል አለፈ። እርሱም: "ምን ሆነው ነው?" አለ። ሰዎችም "ግብር ባለመክፈላቸው ለቅጣት እዚሁ ታስረው ነው።" ብለው መለሱለት። ሂሻምም «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ: "እነዚያን በዱንያ ውስጥ ሰዎችን የሚቀጡን ሰዎች አላህ ይቀጣቸዋል።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት! ወንድ ልጅ ከሌላ ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አይጠቅለል! ሴት ልጅም ከሌላ ሴት ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አትጠቅለል!"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሆነ ብሎ በኔ ላይ የዋሸ ሰው ከእሳት የሆነ መቀመጫውን ያዘጋጅ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مَرَّ عَلَى صُبْرَةِ طَعَامٍ فَأَدْخَلَ يَدَهُ فِيهَا، فَنَالَتْ أَصَابِعُهُ بَلَلًا فَقَالَ: «مَا هَذَا يَا صَاحِبَ الطَّعَامِ؟» قَالَ أَصَابَتْهُ السَّمَاءُ يَا رَسُولَ اللهِ، قَالَ: «أَفَلَا جَعَلْتَهُ فَوْقَ الطَّعَامِ كَيْ يَرَاهُ النَّاسُ؟ @مَنْ غَشَّ فَلَيْسَ مِنِّي».
رواه مسلم