Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:

Available in 48 languages
«ከአቡ ደርዳእ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላግባብ እርግማን የሚያበዛ ሰው ለሁለት ቅጣቶች እንደሚዳረግ ተናገሩ: የመጀመሪያው: የትንሳኤ ቀን መልክተኞች ለህዝቦቻቸው ተልእኳቸውን እንዳደረሱ ከሚመሰክሩ ምስክሮች አይሆኑም፤ አመፀኛ ስለሆነም በዱንያም ምስክርነቱ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሰማዕትነትንም እርሱም በአላህ መንገድ መገደል ስለሆነ አይገጠምም። ሁለተኛው: አማኞች የትንሳኤ ቀን እሳት መግባት ግድ የሆነባቸውን ወንድሞቻቸውን በሚያማልዱበት ጊዜ እነርሱ ግን አያማልዱም።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality