Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 55 languages
«ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ እውነተኛ ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ እውነት ከመናገርና እውነትን ከመምረጥ አይወገድም። አደራችሁን ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል። ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራልና። ሰውዬው አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስኪፃፍ ድረስ ከመዋሸትና ለውሸት ከመጣር አይወገድ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እውነተኝነትን አዘዙ። እውነተኝነትን አጥብቆ መያዝ ለዘውታሪ መልካም ስራና በመልካም ስራ ላይም እንዲዘወትር የሚያደርገው በመሆኑ ሰውዬውን ወደ ጀነት እንደሚያደርሰው ተናገሩ። ሰውዬው እውነት መናገርን በድብቅም ይሁን በይፋ ከመደጋገም እስካልተወገደ ድረስ እጅግ እውነተኛ የሚል ስያሜ ይሰጠዋል። ይህም በእውነተኝነት ላይ ጫፍ የደረሰ ሰው ማለት ነው። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከውሸትና ከቅጥፈት ንግግር አስጠነቀቁ። ይህም ከቀጥተኛው መንገድ ወደ መጣመም፣ ለክፋትና ለወንጀል ስለሚያነሳሳ ነው። ከዚያም ወደ እሳት ያደርሰዋል። ሰውዬውም ውሸትን ከማብዛት እስካልተወገደ ድረስ አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይፃፋል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality