Hadith for the World
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ስነ-ምግባራዊ ፊቅህ

56 hadiths

56 hadiths

ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቢ በክረህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶስት ጊዜ እንዲህ አሉ፦ "'ከትልልቅ ወንጀሎች ትልቁን አልነግራችሁምን?' እኛም 'እንዴታ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!' አልናቸው። እሳቸውም፦ 'በአላህ ማጋራት ፣ የወላጆችን ሐቅ ማጓደል' አሉ። ደገፍ ብለው ከነበረበትም ተስተካክለው ተቀመጡና 'ንቁ! የውሸት ንግግርን (ተጠንቀቁ)።' አሉ። ምነው ዝም ባሉ እስክንል ድረስም ይህንን ከመደጋገም አልተወገዱም።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።"አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ አሕመድ ዘግበውታል።
عن أبي موسى الأشعري رضي الله عنه قَالَ: قالَ رسول اللَّه -صَلّى اللهُ عَلَيْهِ وسَلَّم-: «إِنَّ مِنْ إِجْلاَلِ الله -تَعَالَى-: إِكْرَامَ ذِي الشَّيْبَةِ المُسْلِمِ، وَحَامِلِ القُرْآنِ غَيرِ الغَالِي فِيه، وَالجَافِي عَنْه، وَإِكْرَام ذِي السُّلْطَان المُقْسِط».رواه أبو داود
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعاً: «أتدرون من المفلس؟» قالوا: المُفْلِس فينا من لا دِرهَمَ له ولا مَتَاع، فقال: «إن المفلس من أمتي من يأتي يوم القيامة بصلاة وصيام وزكاة، ويأتي وقد شَتَمَ هذا، وقذف هذا، وأكل مال هذا، وسَفَكَ دم هذا، وضرب هذا، فيعطى هذا من حسناته، وهذا من حسناته، فإن فنيت حسناته قبل أن يُقْضَى ما عليه، أخذ من خطاياهم فَطُرِحتْ عليه، ثم طُرِحَ في النار».رواه مسلم
عن معاذ بن أنس رضي الله عنه مرفوعًا: «مَن كَظَمَ غَيظًا، وَهُو قادر على أن يُنفِذَه، دَعَاه الله سبحانه وتعالى على رؤوس الخَلاَئِق يوم القيامة حتَّى يُخَيِّره من الحُور العَين مَا شَاء».رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!" ሶሓቦችም: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምን ናቸው?" ብለው ጠየቁ፥ ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "በአላህ ማጋራት፣ ድግምት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በአግባቡ ካልሆነ በስተቀር መግደል፣ አራጣ መብላት፣ የየቲምን ገንዘብ መብላት፣ ጦርነት በተፋፋመ እለት ማፈግፈግ፣ ከዝሙት ዝንጉ የሆኑ ጥብቅ ምእመናትን በዝሙት መዝለፍ ናቸው።" አሉ።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه مرفوعًا: «إِنَّ الله تَعَالى يَقُول يَوْمَ القِيَامَة: أَيْنَ المُتَحَابُّونَ بِجَلاَلِي؟ اليَوم أُظِلُّهُم فِي ظِلِّي يَوْمَ لاَ ظِلَّ إِلاَّ ظِلِّي».رواه مسلم
ከሱለይማን ቢን ሱረድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ተቀምጬ ሳለ ሁለት ሰዎች ይሰዳደባሉ። አንዱ ፊቱ ቀልቷል፣ ደም ስሩ ተገታትሯል። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ "እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።" ለርሱም ሄደው "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ" እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም "እኔ ላይ እብደት አለብኝ እንዴ?" አላቸው።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።"ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ሰዎች ጋር የሚበዳደር አንድ ሰውዬ ነበር። ለሰራተኛውም እንዲህ ይለው ነበር፡ 'ምናልባት አላህ እኛንም ይቅር ቢለን የተቸገረ ካጋጠመህ እለፈው።' (ሞተና) አላህንም ተገናኘ፤ አላህም ይቅር አለው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول: «جَعَلَ اللهُ الرحمةَ مائة جُزْءٍ، فَأَمْسَكَ عِنْدَهُ تِسْعَةً وَتِسْعِينَ، وأَنْزَلَ في الأَرْضِ جُزْءًا وَاحِدًا، فَمِنْ ذَلِكَ الجُزْءِ يَتَرَاحَمُ الخَلَائِقُ، حتى تَرْفَعَ الدَّابَّةُ حَافِرَهَا عَنْ وَلَدِهَا خَشْيَةَ أَنْ تُصِيبَهُ». وفي رواية «إِنَّ للهِ تعالى مئةُ رحمةٍ، أَنْزَلَ منها رحمةً واحدةً بَيْنَ الجِنِّ والإنسِ والبَهَائِمِ والهَوَامِّ، فَبِهَا يَتَعَاطَفُونَ، وبها يَتَرَاحَمُونَ، وبِهَا تَعْطِفُ الوَحْشُ على وَلَدِهَا، وأَخَّرَ اللهُ تعالى تِسْعًا وتِسْعِينَ رحمةً يَرْحَمُ بِهَا عِبَادَهُ يومَ القِيَامَةِ». وعن سلمان الفارسي رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «إِنَّ للهِ تعالى مئةُ رحمةٍ فمنها رحمةٌ يَتَرَاحَمُ بها الخَلْقُ بَيْنَهُمْ، وتِسْعٌ وتِسْعُونَ لِيَومِ القِيَامَةِ». وفي رواية: «إِنَّ اللهَ تَعَالَى خَلَقَ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ والأَرْضَ مئةَ رحمةٍ كُلُّ رحمةٍ طِبَاقَ مَا بَيْنَ السَّمَاءِ إلى الأَرْضِ، فَجَعَلَ منها في الأَرْضِ رَحْمَةً فبها تَعْطِفُ الوَالِدَةُ على وَلَدِهَا، والوَحْشُ والطَّيْرُ بَعْضُهَا عَلَى بَعْضٍ، فإذا كانَ يومُ القيامةِ أَكْمَلَهَا بِهَذِه الرحمةِ».حديث أبي هريرة -رضي الله عنه-: متفق عليه. حديث سلمان -رضي الله عنه-: رواه مسلم
‌عَنْ ‌أَبِي ‌ذَرٍّ، ‌جُنْدُبِ ‌بْنِ ‌جُنَادَةَ، ‌وَأَبِي ‌عَبْدِ ‌الرَّحْمَنِ، ‌مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «اتَّقِ اللَّهَ حَيْثُمَا كُنْت، وَأَتْبِعْ السَّيِّئَةَ الْحَسَنَةَ تَمْحُهَا، وَخَالِقْ النَّاسَ بِخُلُقٍ حَسَنٍ».رواه الترمذي
ከነዋስ ቢን ሰምዓን አልአንሷሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ስለበጎ ተግባርና ስለወንጀል ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም " በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።»ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "አትመቀኛኙ፤ (ገዢን ለመጉዳት) አትጫረቱ፤ አትጠላሉ፤ ጀርባ አትሰጣጡ፤ አንዳችሁ በአንዱ ገበያ ላይ አይሽጥ! የአላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ። ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው። አይበድለው፤ እርዳታ አይንፈገው፤ አያሳንሰው።" ወደ ደረታቸው እየጠቆሙም ሶስት ጊዜ "አላህን መፍራት እዚህ ጋር ነው።" አሉ። "ሰውዬው ሙስሊም ወንድሙን አሳንሶ መመልከቱ መጥፎ ሠራ ለመባል ይበቃዋል። ሁሉም ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ደሙ፣ ገንዘቡና ክብሩ እርም ነው።"ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።ቡኻሪ ዘግበውታል።
عن أبي هريرة رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: «لا يُلْدَغُ المؤمنُ من جُحْرٍ واحد مرتين».متفق عليه
ከጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ለስላሳነትን የተነፈገ ሰው መልካምን ተነፍጓል።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عن أنس رضي الله عنه قَالَ: كُنْتُ أمشي مَعَ رسول الله صلى الله عليه وسلم وَعَلَيْهِ بُرْد نَجْرَانيٌّ غَلِيظُ الحَاشِيَةِ، فأدْرَكَهُ أعْرَابِي فَجَبذَهُ بِرِدَائِهِ جَبْذَة شَديدة، فَنَظَرْتُ إِلَى صَفْحَةِ عَاتِقِ النَّبيِّ صلى الله عليه وسلم وَقَدْ أثَّرَتْ بِهَا حَاشِيَة الرِّدَاءِ مِنْ شِدَّةِ جَبْذَتِه، ثُمَّ قَالَ: يَا مُحَمَّدُ، مُر لِي مِنْ مَالِ اللهِ الَّذِي عِنْدَكَ. فَالتَفَتَ إِلَيْهِ، فَضَحِكَ ثُمَّ أَمَرَ لَهُ بِعَطَاءٍ.متفق عليه
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "የአደም ልጅ ሁለት በገንዘብ የሞላ ሸለቆ ቢኖረው ኖሮ ሶስተኛ ሸለቆ ይመኛል። የአደምን ልጅ ሆድ ከአፈር በቀር የሚሞላው የለም። ወደ አላህ ተፀፅቶ በተመለሰ ሰው ላይም አላህ ተውበቱን ይቀበለዋል።"»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ابن عمر رضي الله عنهما مرفوعا: «الظلم ظلمات يوم القيامة». عن جابر رضي الله عنهما مرفوعا: «اتقوا الظلم، فإن الظلم ظلمات يوم القيامة، واتقوا الشُّحَ؛ فإنه أَهْلَكَ من كان قبلكم».حديث ابن عمر -رضي الله عنهما-: متفق عليه. حديث جابر -رضي الله عنه-: رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) የአላህ ባሮች ሆይ! ወንድማማቾች ሁኑ።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊምን መስደብ አመፀኝነት ነው። መግደሉ ክህደት ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ: "ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"ሙስሊም ዘግበውታል።