Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 62 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) የአላህ ባሮች ሆይ! ወንድማማቾች ሁኑ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞች መካከል ወደ ክፍፍልና ጠላትነት ከሚያደርሱ አንዳንድ ነገሮች ከለከሉም አስጠነቀቁም። ከነዚህም መካከል: (ጥርጣሬ) ያለማስረጃ በቀልብ ውስጥ የሚወድቅ መጥፎ እሳቤ ነው። ከወሬዎች ሁሉ እጅግ ውሸት መሆኑን ገለፁ። (መፈላፈል): ይህም በአይን ወይም በጆሮ የሰዎችን ነውር መፈለግ ነው። (መሰለል): ይህም ማለት ድብቅ የሆኑ ነገሮችን መፈለግ ነው። በብዛት ይህ ቃል የሚውለው የሰዎችን መጥፎ ነገር መፈለግን ለማመልከት ነው። (ምቀኝነት): ይህም ማለት ሌሎች ፀጋ ማግኘታቸውን መጥላት ማለት ነው። (ጀርባ መሰጣጠት) : ለሙስሊም ወንድሙ ሰላምታን ላይሰጥና ላይዘይር ከፊሉ ከከፊሉ መዞሩ ነው። (መጠላላት) : ሌሎችን በማስቸገር፣ ፊትን በማጨፍገግና በመጥፎ መስተጋብር በመሳሰሉት ሰዎችን መጥላትና ማሸሽ ነው። ቀጥለውም ሙስሊሞች የእርስ በርስ ሁኔታቸው የሚስተካከልበትን ጠቅላይ ንግግር እንዲህ በማለት ተናገሩ "የአሏህ ባሮች ሆይ!ወንድማማች ሁኑ።" ወንድማማችነት በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚሰበስብ፣ በመካከላቸው መዋደድንና ቅርርብን የሚጨምር ማሰሪያ ገመድ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality